በCambridge ውስጥ በብስክሌት የሚደረጉ ጉዞዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ ነው። በየዕለቱ የገዛ አገልግሎቱን በመጠቀም የሚደረጉ ጉዞዎችን (በሥራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓታት ብቻ ሳይገደብ) የሚከታተለው የBluebikes መረጃ እ.ኤ.አ በ2022 ዓ.ም ከፍተኛውን የጉዞዎች ብዛት መዝግቧል። ወደ ሥራ ቦታ በብስክሌት የሚሄዱ የCambridge ነዋሪዎች ብዛት ከፍተኛው ደረጃ ላይ ደርሶ ከአጠቃላይ የትራንስፖርት አገልግሎቶች 9 በመቶ የሆነ ሲሆን፣ በKendall Square ከሚጓዙ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ውስጥ ደግሞ 9.5 በመቶ የሚሆኑት ብስክሌት ይጠቀማሉ። ብስክሌት የሚጠቀሙ ልጆች ቁጥርም ጭማሪ አሳይቷል።
Cambridge’s Cycling Safety Ordinance በዓይነቱ የመጀመሪያው ድንጋጌ ሲሆን፣ ወደ 25 ማይል ርቀት ያላቸው የተነጣጠሉ የብስክሌት መስመሮች ዝርጋታን እንደ መስፈርት አስቀምጧል። እ.ኤ.አ ሜይ ወር 2024 ዓ.ም እስኪደርስ ከ25 ማይሎች ውስጥ 13.77 ማይሎችን የሚሸፍኑ የብስክሌት መስመሮች የተዘረጉ ሲሆን፣ ባለፉት ሰባት አመታት (ከድንጋጌው በፊት) ከተዘረጉት የተነጠሉ የብስክሌት መገልገያዎች ከ2.5 ማይል በላይ በልጠዋል።
የዚህ ሥራ ዋና ዋና ነጥቦች፦
- የከተማ አስተዳደሩ በBrattle Street የደኅንነት ማሻሻያ ፕሮጀክት አማካኝነት በBrattle Street ላይ Mason Street እና Mount Auburn Street መካከል ባለሁለት አቅጣጫ የተነጠሉ የብስክሌት መስመሮችን ገንብቷል፣ የእግረኛ መሻገሪያዎች ላይ ማሻሻያ አድርጓል እንዲሁም በእግር ለሚጓዙ፣ ብስክሌት ለሚነዱ እና መኪና ለሚያሽከረክሩ ሰዎች ደኅንነት እና ምቾትን አሻሽሏል። Sparks Street እና Mt. Auburn Street መካከል የሚሠራው ሁለተኛ ምዕራፍ እ.ኤ.አ የ2023 ዓ.ም በጋ ወቅት ላይ ተገንብቷል። የከተማ አስተዳደሩ አምስት መስቀለኛ መንገዶች አቅራቢያ የሚገኙ የእግረኛ መሻገሪያዎች ላይ በብስክሌት መስመሮች እና በተሽከርካሪ መንገድ መስመሮች መካከል የእግረኛ ማቋረጫ ደሴቶችንም ገንብቷል።
- የከተማ አስተዳደሩ በHampshire Street የደኅንነት ማሻሻያ ፕሮጀክት አማካኝነት ተጨማሪ የተነጠሉ የብስክሌት መስመሮችን ገንብቶ በInman Square እና The Port/Kendall Square መካከል ይበልጥ አመቺ የሆነ የብስክሌት መስመር ግንኙነት ፈጥሯል። ፕሮጀክቱ ያተኮረባቸው አካባቢዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፦
- ከInman Square እስከ Broadway ድረስ የተዘረጋው የHampshire Street ክፍል
- ከHampshire Street እስከ Portland Street የተዘረጋው የBroadway ክፍል
- Mt. Auburn Street ላይ አዲስ የብስክሌት መሠረተ ልማት ግንባታ ተጠናቅቋል። ይህም የMt. Auburn Street at Aberdeen Avenue Intersection የደኅንነት ማሻሻያ ፕሮጀክት አካል ነበር። ይህ ፕሮጀክት በጎዳናው ሰሜናዊ ጎን የሚገነባውን አዲስ እና የተነጠለ ባለሁለት አቅጣጫ የብስክሌት መስመር፣ የዘመኑ የመንገድ ምልክት መሣሪያዎች እና የተሻሻሉ የትራፊክ መብራት መቀያየሪያ የጊዜ ሰሌዳዎችን እና Homer Avenue እና Aberdeen Avenue ላይ የሚገነቡትን የተራዘሙ የአውቶብስ ብቻ መስመሮችን እና ለሚታጠፉ መኪናዎች ብቻ የሚያገለግሉ አዲስ የመንገድ መስመሮችን ጨምሮ በርካታ ማሻሻያዎችን ያካትታል።
ወደፊት የሚሠራው ሥራ ከOak እስከ Second Street የሚዘረጋው Cambridge Street እና በQuincy Street እና Hampshire Street መካከል የሚዘረጋው እና ከMain Street ጋር የሚገናኘው Broadway ላይ የሚደረጉ ማሻሻያዎችን ይጨምራል።
ከCycling Safety Ordinance ትግበራ ጋር ተያይዞ በሚገነቡ የተነጠሉ የብስክሌት መስመሮች ምክንያት የሚፈጠር የመኪና ማቆሚያ ቦታ ኪሳራን ለመግታት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የከተማ አስተዳደሩ በዚህ የመኸር ወቅት መገባደጃ ላይ በአቅራቢያ ከሚገኙ ንብረቶች ጋር የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን መጋራት እንዲቻል የParking and Transportation Demand Management Ordinance (የመኪና ማቆሚያ እና የትራንስፖርት ፍላጎት ማኔጅሜንት ድንጋጌ) እና የZoning Ordinance (የዞን አደረጃጀት ድንጋጌ) ላይ ሊደረጉ የሚችሉ ማሻሻያዎችን ሊመረምር ይችላል።
- በ1ኛው ዓመት Cambridge 4.19 ማይል የሚሸፍኑ የተነጠሉ የብስክሌት መስመሮችን ግንባታ ጀምሯል ወይም አጠናቅቋል።
- በ2ኛው ዓመት Cambridge 2.15 ማይል የሚሸፍኑ የተነጠሉ የብስክሌት መስመሮችን ግንባታ ጀምሯል ወይም አጠናቅቋል።
- በ3ኛው ዓመት Cambridge 3.67 ማይል የሚሸፍኑ የተነጠሉ የብስክሌት መስመሮችን ግንባታ ጀምሯል ወይም አጠናቅቋል።
- በ4ኛው ዓመት Cambridge 4.21 ማይል የሚሸፍኑ የተነጠሉ የብስክሌት መስመሮችን ግንባታ ጀምሯል ወይም አጠናቅቋል።
የCycling Safety Ordinance ፕሮጀክቶችን ለማግኘት እባክዎን https://camb.ma/csomapን ይጎብኙ።