ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ በከተማ አስተዳደር እና በስቴት ሥልጣን ሥር በነበሩ መንገዶች ላይ 232 ለሞት የዳረጉ ግጭቶች ተከስተዋል። ከነዚህም ውስጥ ብስክሌት እየነዳ የነበረን ሰው ለሞት ከዳረጉ ስምንት አደጋዎች መካከል ሰባቱ የጭነት መኪና ተሳተፈ ነበራቸው።
ይህንን ተከትሎ City Manager Huang እና ሌሎች የተመረጡ የአካባቢ መስተዳድር ባለሥልጣናት እ.ኤ.አ በጁላይ ወር አጋማሽ የስቴቱ Act to Reduce Traffic Fatalities (የትራፊክ አደጋ ሞቶችን ለመቀነስ የወጣ አዋጅ) ላይ ማሻሻያ ለማድረግ የተቀመጡ ደንቦችን በተመለከተ የMassDOT ችሎት ላይ ምስክርነት ለመስጠት Beacon Hill ተገኝተው ነበር።
ይህም Cambridge፣ Boston፣ Somerville እና Newton ከከተሞቻቸው ጋር ለሚሰሩ አቅራቢዎች የጭነት መኪና ደኅንነት መስፈርቶች ያስቀመጡበትን ተመሳሳይ መንገድ ይከተላል። እ.ኤ.አ በኖቬምበር ወር 2020 ዓ.ም በCity Council (የከተማው ምክር ቤት) የፀደቀው የCambridge Truck Safety Ordinance ከ10,000 ዶላር በላይ የሚገመት ውል ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ተፈራርሞ እየሠራ ባለ ከተማዋ ውስጥ የሚገኝ አቅራቢ ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ እና ደረጃ 3 ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ፣ በጠቅላላ የተሽከርካሪ ክብደታቸው ከ10,000 ፓውንድ በላይ የሚመዝኑ እና ከ15 MPH በላይ ፍጥነት መጓዝ የሚችሉ የሞተር ተሽከርካሪዎች፣ ተጎታቾች፣ ባለ ሁለት ጎማ ተጎታቾች ወይም ተሳቢዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል። እነዚህ ደንቦች ከአንዳንድ ልዩ ሁኔታዎች በስተቀር ብቁ የሆኑ ተሽከርካሪዎች በግጭት ጊዜ ተሽከርካሪው ሥር ምንም ነገር እንዳይገባ የሚከላከሉ የጎን መከላከያዎች (ሳይድ ጋርድ)፣ ሰፋ ያለ አካባቢ የሚያሳዩ (ኮንቬክስ) መስታዎቶች፣ የጭነት መኪናውን ፊት ለፊት የሚያሳዩ (ክሮስ-ኦቨር) መስታዎቶች እና አንፀባራቂ የደህንነት ተለጣፊዎች እንዲገጠሙላቸው ያስገድዳሉ።
በስቴቱ የተገዙ፣ በኪራይ የተያዙ ወይም ከስቴቱ ጋር ተዋውለው እየሠሩ ያሉ ከ10,000 ፓውንድ በላይ የሆኑ ተሽከርካሪዎች በግጭት ጊዜ ተሽከርካሪው ሥር ምንም ነገር እንዳይገባ የሚከላከሉ የጎን መከላከያዎች (ሳይድ ጋርድ)፣ ሰፋ ያለ አካባቢ የሚያሳዩ (ኮንቬክስ) መስታዎቶች፣ የጭነት መኪናውን ፊት ለፊት የሚያሳዩ (ክሮስ-ኦቨር) መስታዎቶች እና ምትክ ካሜራዎች እንዲገጠምላቸው የሚጠይቅ የተሽከርካሪ ደኅንነት ደንቦች ማሻሻያን በተመለከተ ከሰጡት ምስክርነት ውስጥ የተወሰደ ቅንጫቢ ከዚህ በታች ቀርቧል። ማሻሻያዎቹን በመደገፍ እና ደንቦቹ በተቻለ መጠን ጠንካራ እንዲሆኑ እና በልዩ ሁኔታ የሚታዩት ተሽከርካሪዎች ቁጥር እንዲቀንስ በመግለጽ ቃላቸውን ሰጥተዋል።
“An Act to Reduce Traffic Fatalities እ.ኤ.አ በ2022 ዓ.ም መፅደቁ ለሁሉም የመንገድ ተጠቃሚዎች እና በተለይም በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ተጠቃሚዎች ጎዳናዎቻችንን ይበልጥ ደኅንነታቸው የተጠበቀ ለማድረግ ወሳኝ እርምጃ ነበር። የዚህን ሕግ ወሳኝ ገፅታዎች ተግባራዊ እያደረጉ ያሉትን የMassDOT የመተዳደሪያ ደንቦች ለውጦችን ለመደገፍ ዛሬ እዚህ በመገኘቴ ደስተኛ ነኝ።
እነዚህ ለውጦች በመንግሥት ባለቤትነት ሥር ለተያዙ እና ለሚንቀሳቀሱ የጭነት መኪናዎች በጣም አስፈላጊ የሆኑ ሲሆን፣ ይህ የመተዳደሪያ ደንብ ለውጥ በእነዚህ የጭነት መኪናዎች እና ተጋላጭ የመንገድ ተጠቃሚዎች መካከል የሚፈጠሩ ከባድ አደጋዎችን ለመከላከል አንድ እርምጃ ወደፊት ያራምደናል። በመጨረሻም በEurope እና በሌሎች ሀገሮች ከ20 ዓመታት በላይ ሲደረግ እንዳየነው ይህ በመንገዶቻችን ላይ ለማሽከርከር ፈቃድ ያገኙ የጭነት መኪናዎችን በሙሉ የሚመለከት ብሔራዊ ስታንዳርድ መሆን አለበት።
በግጭት ጊዜ ተሽከርካሪው ሥር ምንም ነገር እንዳይገባ የሚከላከሉ የጎን መከላከያዎች ላይ በVolpe National Transportation Systems Center የታካሄደው ጥናት እንደሚያሳየው፣ግምገማ ሥር በነበሩት አምስት ዓመታት ውስጥ በጭነት መኪና ከተገደሉት ብስክሌት ነጂዎች ውስጥ ግማሾቹ እና በተመሳሳይ ሁኔታ ከሞቱት እግረኞች ውስጥ አንድ አራተኛ የሚሆኑት መጀመሪያ ከጭነት መኪናው ጎን ጋር ነበር የተጋጩት። UK ውስጥ በግጭት ጊዜ ተሽከርካሪው ሥር ምንም ነገር እንዳይገባ የሚከላከሉ የጎን መከላከያዎች የተገጠመላቸው የጭነት መኪናዎች ዙሪያ የተደረገ ጥናት ከብስክሌት ነጂዎች ጋር በሚፈጠሩ ግጭቶች ላይ የሞት ክስተት በ61 በመቶ መቀነሱን አሳይቷል።
በፌዴራል መረጃ መሠረት ትላልቅ የጭነት መኪናዎች ከተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች 4 በመቶ ያህሉን ይይዛሉ። ሆኖም የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች በደንብ የሰለጠኑ አሽከርካሪዎች ቢሆኑም፣ የጭነት መኪናዎች 10 በመቶ ለሚሆኑት የእግረኛ እና የብስክሌት ነጂ ሞት ምክንያት ናቸው። በሰው እና ትራፊክ በተጨናነቁ የከተማ አካባቢዎች እነዚህ አኃዛዊ መረጃዎች (ስታቲስቲኮች) የበለጠ ከፍ ያሉ ናቸው። ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ሰባት የብስክሌት ነጂዎችን በሞት ያጣን ሲሆን፣ እያንዳንዱ ግጭት ላይ የጭነት መኪና የግጭቱ አካል (ተሳታፊ) ነበር። ይህም በስቴት እና በሀገር አቀፍ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን ከተጋላጭ የመንገድ ተጠቃሚዎች ጋር የተያያዙ አደጋዎች እና ሞቶች ቁጥር የሚተነትን ሰፊ ታሪክ አካል ነው።
ሁላችሁም እንደምታውቁት በሚያሳዝን ሁኔታ በጥቂት ሳምንታት ልዩነት ውስጥ ሁለት ሳይክል እየነዱ የነበሩ ሰዎች ከጭነት መኪና ጋር በተፈጠረ ግጭት ሕይወታቸውን በማጣታቸው ይህ እውነታ በCambridge ውስጥም እንዳለ አስታውሶናል።
በሁለቱም አጋጣሚዎች ብስክሌተኞቹ ከጭነት መኪናዎቹ ጋር ትይዩ በሆኑ አቅጣጫዎች እየተጓዙ የነበረ ሲሆን ለሞት የተዳረጉትም የጭነት መኪናዎቹ ወደቀኝ ለመታጠፍ ሲሞክሩ ነበር። ሁለቱም አደጋዎች አሁንም ምርመራ እየተደረገባቸው ቢሆንም በጭነት መኪናዎቹ ላይ በግጭት ጊዜ ተሽከርካሪው ሥር ምንም ነገር እንዳይገባ የሚከላከሉ የጎን መከላከያዎች እና የጭነት መኪናውን ፊት ለፊት የሚያሳዩ (ክሮስ-ኦቨር) መስታዎቶች ተገጥመው ቢሆን ኖሮ እነዚህን አደጋዎች ሙሉ በሙሉ ለመከላከል ወይም ሞት እንዳይፈጠር ለማድረግ ረድተው ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል። ሕይወታቸውን እና ቤተሰባቸውን ለሚያጡት ሰዎች እና ለማኅበረሰቦቻችን እነዚህ አደጋዎች የሚያስከፍሉት ዋጋ እጅግ አስከፊ ነው።
እነዚህ ደንቦች በተቻለ መጠን ጠንካራ መሆን ያለባቸው ሲሆን፣ ደንቦቹ ላይ ጉልህ ለውጥ ሳይደረግ ረቂቁ ላይ እንደቀረቡት እንዲጸድቁ እናንተን እጠይቃለሁ። በተለይም 'ከእነዚህ ደንቦች ተገዥነት ነፃ የሚሆኑትን ተሽከርካሪዎች ቁጥር መቀነስ' የሚለውን ክፍል 4.10(7) ለምሳሌ እጠቅሳለሁ። በተጨማሪም በChapter 90 ሥር የገንዘብ ድጋፍ በሚደረግላቸው ውሎች ላይ በሙሉ እነዚህን ደንቦች እንድትተገብሩ አጥብቄ አበረታታለሁ። በተቻለ መጠን በርካታ በመንገዶቻችን ላይ የሚገኙ የጭነት መኪናዎች ይህንን አስፈላጊ የደኅንነት መሳሪያ የታጠቁ መሆናቸው ወሳኝ ነው። እነዚህ የደኅንነት ማሻሻያዎች በመላው ስቴት ውስጥ የሚገኙ ተጋላጭ የመንገድ ተጠቃሚዎችን ሕይወት ማሻሻላቸውን ለማረጋገጥ The Commonwealth ልዩ ሚና ይጫወታል። የደንቦቹን አፈፃፀም በተቻለ መጠን ጠንካራ መሆኑን ለማረጋገጥ ተገቢ የሆኑ ሀብቶች እንዲመደቡም ጥያቄ አቀርባለሁ።
የእነዚህ ደንቦች ትግበራ በግጭት ጊዜ ተሽከርካሪው ሥር ምንም ነገር እንዳይገባ ለሚከላከሉ የጎን መከላከያዎች እና ሌሎች የደኅንነት መሳሪያዎች ሁለንተናዊ መስፈርቶችን ለማስቀመጥ በሚደረገው የተቀናጀ ጥረት የመጀመሪያው እርምጃ ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። በጎዳናዎቻችን ላይ የሚጓዝ ሁሉም ሰው ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እና ሁላችንም መሄድ የፈለግንበት ቦታ በሰላም መድረስ መቻላችንን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አብረን ለመስራት በጉጉት እንጠባበቃለን።
በዛሬው ዕለት ስላዳመጣችሁኝ እና ይበልጥ ደኅንነታቸው የተጠበቀ ጎዳናዎችን ለመፍጠር እያገዛችሁ ስለሆነ አመሰግናለሁ።
የጭነት መኪናዎች ከከተማ ሕይወት ሊነጠሉ የማይችሉ ቢሆኑም ለሞት መንስዔ በሚሆኑ አላስፈላጊ እና ተደጋጋሚ ግጭቶች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ መቀነስ የምንችልባቸውን መንገዶች መፈለግ አለብን።
Cambridge ከሌሎች ከተሞች፣ ስቴቶች፣ ኤጀንሲዎች፣ የተመረጡ ባለሥልጣኖቻችን እንዲሁም የአካባቢ እና ብሔራዊ ደኅንነት ተሟጋቾች ጋር በትብብር በመሥራት በፌደራል የጭነት መኪና ደኅንነት ደንቦች ላይ ለውጥ እንዲመጣ የምታደርገውን ጥረት ትቀጥላለች።