እ.ኤ.አ በዲሴምበር ወር 2023 ዓ.ም ላይ Boston፣ Somerville፣ Everett፣ Brookline እና የሥርዓቱ ስፖንሰር የሆነውን Blue Cross Blue Shield of Massachusetts በመቀላቀል Cambridge ተጨማሪ 750 ዘመናዊ ኤሌክትሮኒክ ብስክሌቶችን በክልሉ በሚገኙት የBluebikes ብስክሌቶች ስብስብ ላይ አክላለች። የእነዚህ አዳዲስ ኤሌክትሮኒክ ብስክሌቶች መካተት በመላው 500 ክልላዊ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኘውን አጠቃላይ የBluebikes የብስክሌት ስብስብ እ.ኤ.አ በ2024 ዓ.ም የበጋ ወቅት ወደ 5,000 አሳድጓል።
የክልሉ መደበኛ የብስክሌት መጋሪያ ሥርዓት እንደመሆኑ መጠን ከተመሠረተበት እ.ኤ.አ 2011 ዓ.ም ጀምሮ Bluebikes ያለማቋረጥ ሲስፋፋ ቆይቷል። በተለይ ሞቃታማ በሆኑት የኤፕሪል እና ኦክቶበር ወራት መካከል አጠቃቀም ላይ ጭማሪ ታይቷል
በLyft የሚመረቱት እና በTIME 100 ምርጥ እ.ኤ.አ የ2022 ዓ.ም ፈጠራዎች ውስጥ አንዱ ተብለው የተሰየሙት የBluebikes ኤሌክትሮኒክ ብስክሌቶች የፔዳል-አጋዥ ቴክኖሎጂ ያለው ምቹ አነዳድ፣ ባለአንድ ማርሽ ትራንስሚሽን፣ 60 ማይል መሸፈን የሚችል ረጅም ጊዜ የሚቆይ ባትሪ፣ ለተጠቃሚ ምቹ የሆነ መቆጣጠሪያ LCD (ኤልሲዲ) ስክሪን እና እንደ LED (ኤልኢዲ) መብራት እና አንፀባራቂ ቀለም የመሳሰሉ የደኅንነት ማሻሻያዎችን ይይዛሉ።
የBluebikes ጣቢያ መገኛዎች ጠቋሚ ካርታን https://camb.ma/bbsuggestions ላይ ማግኘት ይችላሉ።
በነፃ የሚሰጡ የብስክሌት አውደ ጥናቶች ላይ ለመሳተፍ ይመዝገቡ https://visitor.r20.constantcontact.com/manage/optin?v=001emHU8ZhrsEZwDFadceLNMCqtlgFElUlN_OPA7GIHD_RCRssSUMauEQMeyPxdqK-tElGjAFf4vi2cZwVLwhtW6TLlO9ZtsRaqOztEYvSDjUOmNG4w2GKPfhDpbI6HK56JwI7ZD12XEhB0NOSMd-CSxQEgyv-u8hkh።