U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

የCambridgeን Bluebikes እና Bike Education ፕሮግራሞች የሚመሩት የቀድሞ መምህር፦ የCommunity Development (የማኅበረሰብ ልማት) ሠራተኛ Tenzin Choephel ታሪክ

ረቡዕ ፣4 ዲሴምበር 2024
" በጣም ከምወዳቸው ነገሮች መካከል ሁለቱ ብስክሌት መንዳት እና ትምህርት ናቸው። "

ለCommunity Development መምሪያ የActive Transportation አስተባባሪ እንደመሆናቸው መጠን Tenzin Choephel የሚጫወቱት ሚና የBluebikes ሥራዎችን፣ ለCambridge ታዳጊዎች የሚሰጡ የብስክሌት ግንዛቤ ማስጨበጫዎችን እና የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄ ለማቅረብ የሚገቡ ጽሑፎችን ጨምሮ በርካታ ነገሮችን ይሸፍናል።

"ለትራንስፖርት አገልግሎት ፍትሐዊነት ትልቅ ተሟጋች" የሆኑት Choephel የሚሠሩት ሥራ ብዙ ሰዎችን መንካት የሚችል በመሆኑ ደስታ የሚሰማቸው ሲሆን፣ Cambridge የትራንስፖርት ተደራሽነት ዕድሎችን ለመፍጠር እንደ ከተማ አስተዳደር የሚሠራውን ጠንካራ ሥራም ያደንቃሉ።

"በተለይ እኛ ከምናቀርበው የincome eligible አባልነት አንፃር Bluebikes እጅግ ለዋጋ ተስማሚ የሆነ አማራጭ ነው" ሲሉ Choephel ይናገራሉ። “አዲስ የBluebikes ጣቢያ ያቋቋምን ጊዜ ግንባታው ካለቀ በኋላ ሰዎች ጣቢያውን ለመጠቀም በሰልፍ መቆም ጀምረዋል። ይህ ደግሞ ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ ምን ያህል እንደሚያስቡ ስለሚያሳይ ኃይለኛ ስሜት ይቀሰቅስብሃል። ‘አሁን በአፓርታማዬ አጠገብ ጣቢያ መኖሩ እጅግ አስደሳች ነው’ ወይም ‘በየቀኑ መኪና መንዳት አያስፈልገኝም’ በማለት ሰዎች እያገኙን ይነግሩናል።"

Choephel የCambridge ከተማ አስተዳደርን ከመቀላቀላቸው በፊት Boston ውስጥ የቴክኖሎጂ መምህር ነበሩ። ሁልጊዜም ከተማሪዎች ጋር አብሮ በመስራት ይደሰቱ የነበረ ሲሆን፣ አስተማሪዎች በሕይወታቸው ላይ ላሳደሩት ተጽዕኖም ትልቅ ቦታ ይሰጡ ነበር። Choephel ከመማሪያ ክፍል ውጭ ሲሆኑ በሰፊው የCambridge አካባቢ ብስክሌታቸውን መንዳት ይወዱ ነበር።

Cambridge ውስጥ ለActive Transportation አስተባባሪነት ክፍት የሥራ ቦታ ሲገኝ Choephel ከችሎታዎቻቸው እና ፍላጎቶቻቸው ጋር የሚጣጣም የሥራ መስክ አድርገው ተመልክተውት ነበር። እ.ኤ.አ ዲሴምበር ወር 2022 ዓ.ም ላይ ቡድኑን ተቀላቀሉ። 

"በጣም ከምወዳቸው ነገሮች መካከል ሁለቱ ብስክሌት መንዳት እና ትምህርት ናቸው" ሲሉ ይናገራሉ።

የCambridge ከተማ አስተዳደር Cambridge ውስጥ ለሚሠሩ ወይም ለሚኖሩ ሰዎች በነፃ በሚያቀርባቸው የብስክሌት ግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ ጥናቶች ኩራት ይሰማዋል። የሁሉም ትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ክፍያ በCambridge ከተማ አስተዳደር የሚሸፈን ሲሆን፣ ለእያንዳንዱ ተሳታፊ በየዓመቱ አንድ የራስ ቁር በነፃ ይሰጣል።

Choephel Safe Routes to School የተሰኘውን የብስክሌት ሥልጠና ፕሮግራም ከተማ አስተዳደሩን ወክለው የሚመሩ ሲሆን፣ ይህ ፕሮግራም በሁሉም የCambridge የመጀመሪያ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የታዳጊዎች ትምህርት ይሰጣል፦ የ2ኛ ክፍል ተማሪዎች የእግረኛ ሥልጠና ያገኛሉ፣ የ4ኛ ክፍል ተማሪዎች የብስክሌት ሥልጠና ያገኛሉ እንዲሁም የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች የመኪና መንገድ ላይ የሚሠጥ የብስክሌት ሥልጠና ያገኛሉ። የእግረኛ ትምህርቶቹ ደኅንነቱ የተጠበቀ የእግር ጉዞ የማድረግ አስፈላጊነትን እና ከእግረኛ መሠረተ ልማት ጋር የተያያዙ መሰረታዊ ነገሮችን ያስተምራሉ። የብስክሌት ደኅንነት ትምህርቱ የራስ ቁር በትክክል መልበስ የሚቻልበትን መንገድ፣ የመኪና ሕግጋትን፣ እንዴት መስቀለኛ መንገዶች እና የመኪና መንገድ መሰናክሎች ውስጥ ደኅንነቱ በተጠበቀ መልኩ መንቀሳቀስ እንደሚቻል እና መሠረታዊ የብስክሌት ጥገና ስልቶችን ያካትታል።

አሁን ያላቸውን ኃላፊነት ከመምህርነት ልምዳቸውን ጋር ማዋሃድ የቻሉት Tenzin በተለይ ብስክሌት ለመንዳት አዲስ የሆኑ ልጆችን መርዳት ያስደስታቸዋል።

“ብዙ ተማሪዎችን ብስክሌት አነዳድ አስተምሬያለሁ” ሲሉ Choephel ይናገራሉ። “በሥራዬ ካጋጠሙኝ በጣም ጣፋጭ ጊዜዎች መካከል ብስክሌት መንዳት የሚችሉ ልጆችን ብስክሌት መንዳት ከማይችሉ ጓደኞቻቸው ጋር ያሰለጠንኩባቸው ጊዜያት ይጠቀሳሉ። ሁሉም በአንድ ላይ ብስክሌቶቻቸውን እየነዱ ወደ ፓርክ መሄድ እንዲችሉ ጓደኞቻቸው እንዲሳካላቸው ስለሚፈልጉ ከጎን ሆነው ያበረታቷቸዋል። ሲገጣጠም በጣም ነው ደስ የሚለው።"

በCambridge መኖር የጀመሩት በቅርቡ ከሆነ እና ብስክሌተኛ የመሆን ፍላጎት ካለዎት፣ ስለ ብስክሌት ደኅንነት ተጨማሪ ነገር ማወቅ ከፈለጉ፣ የራስ ቁር ካስፈለግዎት ወይም ደግሞ ስለ Bluebikes እና ብስክሌት ስለመንዳት ማውራት ከፈለጉ Tenzin ከእርስዎ ጋር ለመገናኘት በጉጉት ይጠብቃሉ። በማንኛውም ጊዜ በtchoephel@cambridgema.gov ኢሜይል ይላኩላቸው።  

Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here