የከተማ አስተዳደሩ በእግር ከመጓዝ፣ ብስክሌት ከመንዳት እና የሕዝብ ትራንስፖርት አማራጮችን ከመጠቀም ጎን ለጎን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (EV) መሠረተ ልማትም አስፈላጊ መሆኑን ይገነዘባል። የከተማ አስተዳደሩ በመላው Cambridge ውስጥ የሚገኙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አቅርቦት መሣሪያዎችን (EVSE) በመደገፍ በነዳጅ ከሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሚደረገውን ሽግግር በማመቻቸት ላይ ይገኛል።
ወደ 40 የሚጠጉ በከተማ አስተዳደሩ ባለቤትነት የተያዙ ቻርጅ ማድረጊያዎች በመላው Cambridge ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የEV ቻርጅ ማድረጊያ አውታራችንን ለማስፋፋት እየሠራን ነው። የከተማ አስተዳደሩ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያዎችን ተደራሽነት ለማሳደግ እና የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀቶችን ለመቀነስ ግቦች አስቀምጧል። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያዎችን መገንባት እነዚህን ግቦች እንድናሳካ ይረዳናል። እ.ኤ.አ በ2024 እና 2025 ዓ.ም ቻርጅ ማድረጊያ ሊገጠምባቸው የሚችሉ የተወሰኑ ቦታዎችን ለይተናል።
የከተማ አስተዳደሩ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ ለማድረግ ከመንገድ ውጪ የሆነ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ለሌላቸው ነዋሪዎችም የጊዜያዊ ፈቃድ አሰጣጥ ፕሮግራም አዘጋጅቷል። ነዋሪዎች በኦንላይን ማመልከቻ በኩል ዓመታዊ ፈቃዱን፣ የሚያስከፍለውን ክፍያ፣ መስፈርቶቹን እና ለማመልከቻው ብቁ የሆኑ ቦታዎችን በተመለከተ የበለጠ ማወቅ ይችላሉ። ማሳሰቢያ፦ እርስዎ መንገድ ዳር ከሚገኝ በከተማ አስተዳደሩ ባለቤትነት ሥር የተያዘ ነባር የEV ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ ከ1/8ኛ ማይል ያነሰ ርቀት ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ከሆነ ለጊዜያዊ ፈቃድ ማመልከቻው ብቁ አይደሉም።
Cambridge ውስጥ ብቻ ተፈጻሚ የሚደረገው እና እ.ኤ.አ ዲሴምበር ወር 2022 ዓ.ም ላይ በገዥው ፊርማ የጸደቀው The Right-to-Charge ሕግ ኮንዶሚኒየም ውስጥ ወይም ብዙ ቤተሰቦች የሚኖሩበት ሕንፃ ውስጥ የሚኖሩ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባለቤቶችን ታሳቢ በማድረግ የተነደፈ ነው። ይህ ሕግ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባለቤቶች በሚኖሩበት ሕንፃ ላይ በሕንፃው ባለቤት ወጪ የEV ቻርጅ ማድረጊያዎችን እንዲገጥሙ መብት ይሰጣል። የEV ቻርጅ ማድረጊያ ሥርዓቶች ፈቃድ እና ብቃት ባለው የኤሌክትሪክ ባለሙያ ወይም ሥራ ተቋራጭ መገጠም ይኖርባቸዋል።