The Cambridge Police Department (CPD) (የCambridge የፖሊስ አገልግሎት መምሪያ) በCambridge ውስጥ እና Cambridgeን አልፈው በሚጓዙ ግለሰቦች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እና እንደ የCPD እና የከተማ አስተዳደሩ የVision Zero ቃል ኪዳን አካል የመኪና መንገድ ተጠቃሚዎችን በሙሉ ስለ መንገድ ደኅንነት ግንዛቤ ለማስጨበጥ ትምህርት እና ሕጋዊ ማስፈጸሚያዎችን ተግባራዊ ያደርጋል። ትምህርት እና ሕጋዊ ማስፈጸሚያዎች ተግባራዊ የሚደረጉባቸው ቦታዎች የሚወሰኑት በግጭት መረጃ፣ በማኅበረሰብ አስተያየት እና ከሌሎች የከተማ አስተዳደር ኤጀንሲዎች ጋር በመቀናጀት ነው።
የሕጋዊ ማስፈጸሚያዎች የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል በፍጥነት ማሽከርከር፣ አደንዛዥ ንጥረ ነገር ተጠቅሞ ማሽከርከር፣ የመታጠፊያ ገደቦች፣ በተከለከሉ መንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሱ የጭነት መኪናዎች፣ የብስክሌት መስመር ጥሰቶች፣ የብስክሌት አነዳድ ጥሰቶች፣ የአውቶቡስ መስመር ጥሰቶች፣ ትኩረት የጎደለው ማሽከርከር እና የቀይ መብራት/የአቁም ምልክት ጥሰቶችን ይካተታሉ። በተጨማሪም የፖሊስ መኮንኖች በታዘቡት የብስክሌት ነጂዎችን እና/ወይም እግረኞችን አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውም ጥንቃቄ የጎደለው ባህሪ ላይ ማተኮር እንዲችሉ CPD በየዓመቱ የድጎማ ገንዘብ ይበረከትለታል። በትራፊክ እና በመንገድ ደኅንነት ዙሪያ ያሉ ትምህርታዊ ጥረቶች በግጭት ለሚደርሱ ጉዳቶች እና የትራፊክ መጨናነቆች በተደጋጋሚ አስተዋፅኦ በሚያደርጉ ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች እና የትራፊክ ሕግ ጥሰቶች ላይም ያተኩራሉ።