U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

የሠራተኛ መረጃ ማጠቃለያ፦ የማኅደረ አያያዝ ባለሙያዋ ለCambridge ታሪክ ሕይወት ሰጡ

ሰኞ ፣17 ማርች 2025
" የቤተ መጻሕፍቱ ማኅደሮች የእነዚህን ማኅበረሰቦች ወሳኝ ታሪኮች ሊወክሉ፣ በCambridge ታሪክ ላይ ያላቸውንም ጉልህ ተሳትፎ ሊያንጸባርቁ ይገባል። "

የCambridge Public Library ዋና ቅርንጫፍ 2ኛ ፎቅ ላይ ልዩ ዕንቁ ይገኛል። Cambridge Room የማኅደር አያያዝ እና ከፍተኛ የቤተ መጻሕፍት ባለሙያ በሆኑት Alyssa Pacy የተዋቀሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የCambridge ታሪኮች የሚገኙበት ክፍል ነው።

Pacy የቤተ መጻሕፍቱ የመጀመሪያው የማኅደር አያያዝ ባለሙያ ሲሆኑ፣ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮም የቤተ መጻሕፍቱን የመጀመሪያዎቹን ማኅደሮች ሀ ብለው የማዋቀራቸውን ሥራ ሲሠሩ ቆይተዋል። የቤተ መጻሕፍቱ ስብስብ ቀደም ሲል ቤተ መጻሕፍቱ ከመታደሱ በፊት በአሮጌው ቤተ መፃህፍት ህንጻ ውስጥ ይኖሩ የነበረ ቢሆንም፣ እዚያ ስለነበረው ነገር ግን ምንም ዓይነት ትክክለኛ የመዝገብ አያያዝ አሠራር እንዳልነበረ፣ የነበሩትም መዝገቦች በጣም ውስን እንደሆኑ ይናገራሉ።

“እዚህ ሥራ ስጀምር፣ የእድሳት ሥራው እየተሠራ ስለነበር ሁሉም ነገር ሳጥን ውስጥ ገብቶ መጋዘን ነበር የነበረው፣ ከዚያም ሕፃው ሲከፈት ሁሉንም ሳጥኖች አስገቧቸው እና ሥራ ጀመርኩኝ፤ ምንም ነገር አልነበረም። የማይታመን ነበር” ሲሉ Pacy ተናግረዋል። “እዚህ ምን እንደነበር ማወቅ ነበረብኝ። ስብስቡ ውስጥ ምን እንደነበር የማውቀው ነገር አልነበረኝም። እውነተኛ የሚባሉ ክፍተቶችም ነበሩ።"

ወዲያውኑም Pacy ነባር ስብስቦቹ ነጭ፣ ወንድ የHarvard ግንኙነት የነበሯቸውን ነዋሪዎች ብቻ በዋናነት እንደሚወክሉ አስተዋሉ። ጥቁር ማኅበረሰቦችን የሚደግፉ ምንም ድርጅቶች ያልተካተቱበት ሁኔታ የነበረ ሲሆን፣ የሴቶች መብት ተሟጋች ቡድኖች፣ የስደተኛ ቡድኖች እና የLGBTQ+ አክቲቪዝቶችም ውክልና ያንሳቸው ነበር። ይህንን ለመለወጥ ቆርጠው ተነሱ።

“ብዙውን ጊዜ በማኅበረሰብ ውስጥ የግንኙነት ግንባታ ሥራ እየገነባው እገኛለሁ፣ ምክንያቱም ደግሞ በእነዚህ ማኅበረሰቦች ላይ እምነት መገንባት ስላለብኝ ሲሆን በተለይ ደግሞ በቤተ መጻሕፍት ስብስብ ረገድ ችላ ተብለዋል” ብለው ተናግረዋል።

ምንም እንኳን በተለምዶ የሚገባቸውን አገልግሎት ካላገኙ ማኅበረሰቦች ጋር መተማመንን መፍጠር ከባድ ሊሆን ቢችልም፣ የቤተ መጻሕፍቱ ማኅደሮች ግን እነዚህን ማኅበረሰቦች በCambridge ታሪክ የተጫወቱን ወሳኝ ሚና መወከል አለባቸው።

"Cambridge ውስጥ ያለው ጥቁር ማኅበረሰብ በመሠረቱ ከመጀመሪያው ጀምሮ እዚህ ነበር። በተለምዶ በጣም ትንሽ ነገር ግን በጣም አቅም ያለው ማኅበረሰብ የነበረ ሲሆን፣ ልዩ የሚያደርገው ደግሞ America ውስጥ ከሚነሱ ዋና ዋና የፖለቲካ እና የባህል እንቅስቃሴዎች ጋር በተደጋጋሚ መገናኘቱ ነው” ሲሉ Pacy ፓሲ ተናግረዋል። “በጣም የሚያስደንቅ፣ አነስ ያለ ነገር ግን ትልቅ አቅም ያለው ማኅበረሰብ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ በሰነዶች ተቀምጦ ለሕዝብ ይፋ አለመደረጉ ያሳዝናል። ስለዚህ እኔ እነዚህን ክፍተቶች መሙላት መቻሌ ቁልፍ ነው።"

ስብስቦችን ከማዘጋጀት ባሻገር፣ Pacy በማኅደር የተቀመጡ ቁሳቁሶችን እና መረጃዎችን የመመዝገብ፣ የመጠበቅ፣ የማውጣት እና ዲጂታል የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው። ሰፊው የዲጂታል ስብስቦች ከCambridge ጋዜጦች የተገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጽሑፎችን እና ከበርካታ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የዓመቱ ማገባደጃ መጽሐፎችን እና ሌሎች በርካታ ሰነዶችን ያካተቱ ናቸው። በኦንላይን ወይም በአካል ስብስቦችን ለማግኘት ከሚፈልጉ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ተመራማሪዎች ጋርም እየሠሩ ይገኛሉ።

"በዓመት ወደ 600 ለሚጠጉ በርቀት ለሚጠየቁ ማመሳከሪያ ጥያቄዎች ምላሽ እሰጣለሁ። እነዚህ ጥያቄዎች ምን ዓይነት ሊሆኑ ይችላሉ ለምሳሌ 'የቤቴን ታሪክ ማወቅ እፈልጋለሁ' ከማለት 'የሟቾች የሕይወት ታሪክ' እስከመጠየቅ እና 'በኦንላይን የሚገኘውን ታሪካዊ የጋዜጣ ስብስብ ተደራሽነትን ማግኘት እፈልጋለሁ' እስከማለት ድረስ ሊደርሱ የሚችሉ ጥያቄዎች ሊካተቱባቸው ይችላሉ” ሲሉ Pacy ተናግረዋል። “በዚህ ሳምንት ያገኘሁት አስገራሚ ጥያቄ ‘ስለ መቃብር ቆፋሪዎች እና አስክሬን አውጪዎች መረጃ እየፈልጋለሁ’ የሚል አንድ ጥያቄ ነበር። ስለዚህ ርዕሶቹ እግጅ ሰፉ እና በዓይነት የተለያዩ ናቸው።"

ከዚህም በተጨማሪ Pacy Cambridge ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች ቡድኖች እና ድርጅቶች ጋር በበርካታ ፕሮጀክቶች ላይ እየሠሩ ይገኛሉ። በቅርብ ጊዜ ከሠሩት የሚወዱት አንዱ ፕሮጀክት ከአርቲስት Elisa Hamilton እና ከCambridge Black History ፕሮጀክት ጋር የሠሩት ፕሮጀክት ነው። Hamilton ሙዚቃ ማጫወቻ ሳጥን የሠራ የነበር ሲሆን፣ ቆየት ያለውን የሙዚቃ ማጫወቻ ሳጥን Foundry ውስጥ ተቀምጦ የማኅበረሰቡን ታሪኮች የሚያጫውት የሕዝብ የሥነ ጥበብ ሥራ እንዲሆን አድርጎ ሠርቶታል። የBIPOC ማኅበረሰብ ታሪኮች በዚህ ፕሮጀክት መካተቱን ማረጋገጥ አርቲስቷ ፈልጋ የነበር ሲሆን፣ Pacy ደግሞ የCambridge ጥቁር ማኅበረሰብ ታሪክን ለመመዝገብ የጥናት እና ምርምር ሥራ ከሚሠሩት እና የማኅደሩ የዘወትር ተጠቃሚዎች ከሆኑት Cambridge Black History ፕሮጀክት ጋር ትውውቅ እንዲፈጥሩ አድርገዋል።


Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here