የCambridge Fire የ2024 ዓ.ም የአደጋ ምላሽ ቁጥሮች ቅኝት
ሰኞ ፣17 ማርች 2025
California ውስጥ ጃኑዋሪ ወር 2025 ዓ.ም ላይ ያጋጠሙት የሰደድ እሳቶች ሀገሪቷን እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ያሉ በርካታ ሰዎችን አስገርመዋል። በLos Angeles ዙሪያ ባሉት ትልልቅ አካባቢዎች የተከሰቱትን አስቸጋሪ የእሳት ነበልባሎች ለማጥፋት በጀግንነት ሲታገሉ ለነበሩት የእሳት አደጋ ሠራተኞችም የነበረንን አድናቆት ከፍ አድርገውታል።
Cambridge ውስጥ እንደነዚህ ዓይነት ብቁ ሥልጠና ያላቸው እና ሥራቸውን የሚወዱ የእሳት አደጋ ሠራተኞች ስላሉን ዕድለኞች ነን። 2024 ዓ.ም ላይ እንደገና ሥራ በዝቶባቸው ነበር። በጠቅላላ Cambridge ለ16,182 የአደጋ ጥሪዎች ምላሽ የሰጠ ሲሆን፣ እያንዳንዱ የእሳት አደጋ ድርጅት ደግሞ ለ36,330 የአደጋ ጥሪዎች በተናጠል ምላሽ ሰጥቷል።
ከእነዚህ ምላሾች ውስጥ ለ54 የሕንፃ እሳት አደጋዎች፣ 1,000 የውስጥ እሳቶች፣ 1,148 ሁሉም ዓይነት ምድቦች ውስጥ ለሚካተቱ እሳት አደጋዎች፣ 7,387 የሕክምና አደጋዎች፣ 237 የአሳንሰር (ሊፍት) አደጋዎች፣ 77 የካርቦን ሞኖክሳይድ መበከል አደጋዎችን ጨምሮ ለሌሎች አደጋዎች የተሰጡ ጥሪዎችም ይካተቱባቸዋል። 2024 ዓ.ም ላይ የCambridge እሳት አደጋ ድርጅቶች በአከባቢው የሚገኙ ማኅበረሰቦችን ለማገዝ 196 ጊዜ ከከተማው ውጭ ላጋጠሙ አደጋዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
ካጋጠሙት አደጋዎች መካከል እጅግ አስከፊዎቹ ጃኑዋሪ ወር ላይ North Cambridge ውስጥ በጣም በጠዋት ያጋጠመው 3ኛ ደረጃ ማንቂያ ውስጥ የተመደበው እና የአንድ ነዋሪ ሕይወት የቀጠፈው እሳት ይጠቀሳል፤ ኤፕሪል ወር ላይ ብዙ መኖሪያ ቤቶች በሚገኙበት የBroadway አንድ አካባቢ ላይ ያጋጠመው 2ኛ ደረጃ ማንቂያ ውስጥ የተመደበው እሳት ይጠቀሳል፤ ኦክቶበር ወር ላይ Concord Turnpike ውስጥ በሚገኝ አንድ ባለ 6 ፎቅ መኖሪያ ሕንፃ ላይ ያጋጠመው 2ኛ ደረጃ ማንቂያ ውስጥ የተመደበው እሳት ይጠቀሳል፤ እንዲሁም በአንድ ቀዝቃዛ ኦክቶበር ምሽት Kirkland Street ላይ በሚገኝ አንድ ትልቅ አፓርታማ ሕንፃ ላይ የተፈጠረው 2ኛ ደረጃ ማንቂያ ውስጥ የተመደበው እና አንድ ግለሰብ እንዲሁም ድመቱ በእሳት አደጋ ሠራተኞች በአየር ላይ መሰላሎች አማካኝነት የዳኑበት እሳት ይጠቀሳል።
የእያንዳንዱን የአከባቢ የእሳት አደጋ ድርጅት የአደጋ ምላሽ መረጃዎችን በተናጠል ማየት ከፈለጉ ወደ https://www.cambridgema.gov/cfd/aboutus/firestatistics ድር-ገጽ ይሂዱ።