የCambridge Urban Forestry Division (የCambridge ደን ልማት መምሪያ ክፍል) የ2024 ዓ.ም ትላልቅ ምዕራፎችን አበሠረ
ሰኞ ፣17 ማርች 2025
የCambridge Department of Public Works የደን ልማት መምሪያ ክፍል የከተማ አስተዳደሩ የከተማውን የደን ጥላ ሽፋን ለመጨመር እና ጠብቆ ለማቆየት ያለውን ቁርጥ አቋም ከግብ ለማድረስ የሚያስችሉ ትልቅ ሥራዎች ሠርቷል።
2024 ዓ.ም ላይ በከተማው ዙሪያ 1,250 አዲስ ዛፎች የተተከሉ ሲሆን፣ የአከባቢውን አረንጓዴ ስፍራዎች በማሻሻል እና ወሳኝ የከባቢ አየር ጥቅሞችን በመስጠት ረገድ ትልቅ አስተዋጽዖ አድርገዋል። የእነዚህ ዛፎች የማበብ ምጣኔ ከፍተኛ መሆኑን መምሪያ ክፍሉ ሪፖርት ያደረገ ሲሆን፣ በስፕሪንግ (መኸር) ወቅት የሚተከሉ ዛፎች የሞት ምጣኔም 3.5 በመቶ ብቻ መሆኑን ገልጿል፤ ይህም ለዛፎቹ የሚደረገው ጥንቃቄ የተሞላበት እንክብካቤ እና ጠብቆ የማቆየት ሥራ ስኬታማ መሆኑን ያንጸባርቃል።
ኮንክሪት እና አስፋልት ቦታዎች የማስወገድ ሥራው የችግኝ ተከላ እድሎችን በማሳደግ ረገድም ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። 45 አዲስ ዛፎች እንዲተከሉ ለማድረግ አስፋልት፣ ብሎኬት እና ኮንክሪትን ጨምሮ 5,000 ስክዌር ጫማ የሚሆን ደረቅ ስፍራ ተነስቶ፣ አሸዋማ እና ለም በሆነ አፈር እንዲቀየር ተደርጓል። ይህ ተነሳሽነት ለከተማዋ አረንጓዴ መሠረተ ልማት አስተዋጽዖ ከማድረግ ባለፈ፣ በከተሞች የሚያጋጥመው የሙቀት ችግር ለመቀነስ እና የዝናብ ውኃ ፍሰት አስተዳደርን ለማሻሻል ይረዳል።
መምሪያ ክፍሉ መሬት ላይ ከሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ Cambridge Urban Forest Friends የተሰኘውን ጋዜጣ ከእንደገና ሥራ በማስጀመር፣ 2024 ዓ.ም ላይ የ105 በመቶ የደንበኛ ተመዝጋቢ እድገት አስመዝግቧል። ይህ በአዲስ መልክ ከእንደገና ሥራ የጀመረው ምናባዊ (ቨርቹዋል) ጋዜጣ ለማኅበረሰቡ ከዛፍ ጋር ተያያዥ የሆኑ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትምህርታዊ መረጃዎችን እና የCambridge የከተማ ደኖችን በመጠበቅ ሥራ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑባቸውን መልካም አጋጣሚዎች ለማሳወቅ እየሠራ ይገኛል።
የከተማችንን ደን ለመንከባከብ እገዛ ማቅረብ የሚሹ ነዋሪዎች Urban Forest Friend በመሆን ወይም ወደ CambridgeMA.gov/UrbanForestry ድር-ገጽ በመሄድ ለጋዜጣው በመመዝገብ እገዛቸውን እንዲቸሩ እናበረታታለን።