የኮሌጅ ስኬት ተነሳሽነት 10ኛ ዓመቱን አከበረ
ሰኞ ፣17 ማርች 2025
"
ታሪክን ስንቃኝ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ውክልና የሚያንሳቸው የከተማው ነዋሪዎች በኮሌጅ ስኬት ተነሳሽነት በኩል እርዳታ ያገኛሉ
"
ከ360 በላይ የCambridge ነዋሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ግቦቻቸውን እንዲከተሉ በመደገፍ ያሳለፋቸውን 10 ዓመታት ላከበረው የኮሌጅ ስኬት ተነሳሽነት (CSI) 2024 ዓ.ም ጉልህ የሆነ ምዕራፍን አመላክቷል። ከDepartment of Human Service Programs ውስጥ የሚንቀሳቀሰው CSI ስደተኞችን፣ የመጀመሪያ ትውልድ ተማሪዎችን እና ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች የሚመጡ ተማሪዎችን ጨምሮ ታሪክን ስንቃኝ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ውክልና የሚያንሳቸው የCambridge ነዋሪዎች የኮሌጅ ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁበትን ምጣኔ ለመጨመር የተፈጠር ነው።
CSI ዒላማ የሚያደርጋቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች የCambridge Rindge እና የLatin ትምህርት ቤት መደበኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተመራቂዎችን፣ ከማኅበረሰብ ትምህርት ማዕከሉ Bridge to College ፕሮግራም እየተሸጋገሩ የሚገኙ አዋቂ ተማሪዎችን እና ከJust-A-Start YouthBuild ፕሮግራም የተመረቁ ታዳጊ ወጣቶችን ያካትታሉ። CSI በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ከተመዘገቡ በኋላ ባሉት 6 ዓመታት ውስጥ የድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ዲግሪ (የኮሌጅ ዲፕሎማ ወይም ባችለር ዲግሪ) በማጠናቀቅ ረገድ እነዚህን ተማሪዎች ለመደገፍ የተቀረጸ ነው።
ለተማሪዎች የሚያቀርበው ድጋፍ በግለሰብ ደረጃ በመሆኑ የCSI ሞዴሉን ልዩ ያደርገዋል። እያንዳንዱ የCSI ተማሪ የትምህርት ሥርዓቱን ለመረዳት እና በውስጡ ለመንቀሳቀስ የሚረዳቸው፣ ማኅበረሰባዊ ግብዓቶች ወደሚገኙበት የሚጠቁማቸው እና በትምህርት ክፍል ውስጥ እና ከትምህርት ክፍል ውጪ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ለማግኘት ጥያቄ እንዲያቀርቡ የሚደግፋቸው የኮሌጅ ስኬት አሰልጣኝ ይመደብላቸዋል።
ተጨማሪ ለማወቅ https://www.cambridgema.gov/collegesuccess ድር-ገጽን ይጎብኙ።