የCommunity Safety Department የ9-1-1 ምላሽ ሰጪ አገልግሎት መጀመሩን አስከትሎ በማኅበረሰብ ውስጥ አፋጣኝ ለውጥ ማምጣት ችሏል
ሰኞ ፣17 ማርች 2025
ለበርካታ ዓመታት ከዘለቁ ውይይቶች፣ ቅስቀሳዎች፣ ዕቅዶች እና ትጋት የተሞላባቸው ሥራዎች በኋላ 2024 ዓ.ም ላይ የCommunity Safety Department CARE ቡድን የ9-1-1 ምላሽ ሰጪ እና ድጋፍ አገልግሎቶቹን ለማኅበረሰቡ አስጀምሯል። ይህ ከእንደገና እንደ አዲስ የተዋቀረው ኤጀንሲ በጥሩ ሁኔታ የሠለጠኑ፣ ሩህሩህ እና ቁርጠኛ የሆኑ፣ የጦር መሣሪያ ያልታጠቁ ሲቪል ዜጋዎችን በማብቃት፣ ከአእምሮ ጤና ቀውስ ጋር ተያያዥ ላልሆኑ ጥሪዎች ምላሽ እንዲሰጡ፣ ለደኅንነት እና ለኑሮ ጥራት ደረጃ ፍተሻዎች እንዲሠማሩ፣ ከወንጀል ነክ ጉዳዮች፣ ምርመራዎች ወይም ግድያዎች ጋር ተያያዥ ላልሆኑ አስቸኳይ ጉዳዮች ማሳወቂያዎችን እንዲያደርሱ እና ለሌሎች ጉዳዮችም ምላሽ እንዲሰጡ አስችሏል።
አገልግሎት ከተጀመረ ብዙም ሳይቆይ በአከባቢው በሚገኝ አንድ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ የማኅበረሰቡ አባል የሆነ አንድ ግለሰብ ከአእምሮ ጤና ጋር የተያያዘ ችግር እያጋጠመው እንደሆነ የሚገልጽ ጥሪ ደረሰ። CARE ቡድኑ የማኅበረሰቡን አባል በቦታው ተገኝቶ መርዳት የቻለ ሲሆን፣ First Step ከተሰኘው ለከተማ አስተዳደሩ የመጠለያ እና የአእምሮ ጤና አገልግሎቶችን የመሳሰሉ አቅርቦቶች በማገናኘት ከሚያግዘው ድርጅት ጋር በነበረው ጠንካራ ግንኙነት አማካኝነት በአካባቢው በሚገኝ አንድ መጠለያ ውስጥ የማኅበረሰቡ አባል ቦታ እንዲያገኝም አድርጓል።
በቅርብ ለጥሪዎች ከተሰጡ ምላሾች መካከል በአንዱ፣ አንድ የማኅበረሰቡ አባል የሆኑ ግለሰብ በጠየቁት እገዛ መሠረት ወደ ማገገሚያ (ዲቶክስ) ተቋም እንዲገቡ፣ በተቋሙም አልጋ እንዲያገኙ እና ለማገገም የሚያስፈልጋቸውን ሕክምና እንዲከታተሉ ማድረግ ተችሏል። የCARE ቡድኑ ሠራተኞች መጀመሪያ በቦታው ሲገኙ ይህን የማህበረሰብ አባል በአንድ የመኖሪያ ቤት ደረጃ ላይ ተቀምጦ፣ ዕፆችን አላግባብ ከመጠቀም ጋር የተያያዘ ችግር እያጋጠመው ሳለ ነበር ያገኙት። ይህ የማኅበረሰቡ አባል ከዚህ ቀደም ስኬታማ ወደነበሩበት፣ ባለባቸው ችግር ግን የቅበላ ሂደቱን በራሳቸው አልፈው፣ ተቋሙ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መግባት ያልቻሉበት ሁኔታ ተፈጥሮ ወደነበረበት የማገገሚያ ተቋም ገብተው፣ ድጋፍ የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው ይፈልጉ ነበር። የCARE ቡድኑ ሐኪም የትራንስፖርት እና የሪፈራል ዕቅድ አማራጮች አመዛዝነው፣ በስተመጨረሻ የማኅበረሰቡን አባል ተቀባይነት በተሳካ ሁኔታ ማመቻቸት ችለዋል።
በ2024 ዓ.ም መገባደጃ ላይ ወደ 1,600 የሚጠጉ መርፌዎች ከመንገዶቻችን እና ከመናፈሻዎቻችን እንዲወገዱ ምክንያት የሆኑትን የመርፌ ማስወገድ ጥሪዎች ሳይጨምር የCARE ቡድኑ ወደ 200 የሚሆኑ የ9-1-1 ጥሪዎችን እንዲያስተናግድ ተሠማርቶ ነበር። ችግሮችን ለመፍታት በሚያከናውኗቸው ሥራዎች 160 የሚጠጉ የማኅበረሰብ አባላትን አገልግለዋል። በግምት 94 በመቶ የሚሆኑት ጥሪዎቻቸውም የፖሊስ ተሳትፎ የሚያስፈልጉባቸው ሁኔታዎችን ቀንሰዋል።
በተጨማሪም የCARE ቡድኑ የጉዳይ አስተዳደር እና ሪፈራል አገልግሎት ለማቅረብ ከማኅበረሰቡ አባላት ጋር ይሠራል። ከ2024 ዓ.ም ስፕሪንግ (መኸር) ወቅት ጀምሮ የCARE ቡድኑ 60 ለሚሆኑ የማኅበረሰቡ አባላት ቀጣይነት ባለው መልኩ አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል። የጉዳይ አስተዳደር አገልግሎቶች የሚባሉት የመኖሪያ ቤት ፍለጋ አገልግሎትን፣ የምግብ ዋስትና እጦት መፍታትን፣ ከቤት ማስለቀቅ ሂደት ጋር ተያያዥ የሆነ እገዛን፣ ስሜታዊ ድጋፍ ማቅረብን፣ የአጋር ድርጅቶች ሪፈራል መስጠትን እና ለሌሎች መሠረታዊ ፍላጎቶች የሚደረጉ ድጋፎችን እና አገልግሎቶችን ያካትታሉ። ከዚህ በተጨማሪ CARE ቡድኑ የማኅበረሰቡን አባላት ለመደገፍ አከባቢው ላይ ከሚገኙ እንደ Salvation Army እና Christ Church Cambridge ከመሳሰሉ ድርጅቶች ጋር ጠንካራ ግንኙነቶችንም ፈጥሯል።
የCambridge Police Department (የCambridge ፖሊስ መምሪያ) ከCambridge Community Safety Department CARE ቡድኑ ጋር በቅርበት ሲሠሩ ቆይተዋል። ይህ አዲስ ግብዓት የCambridge ከተማ አስተዳደር አጠቃላይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራውን ለማሳደግ ለመርዳት የሚያስችል መልካም አጋጣሚ ነው ሲሉ የፖሊስ ኮሚሽነር Christine Elow ተናግረዋል። "የፖሊስ መኮንኖቻችን በየቀኑ ብዙ ኃላፊነቶች ያሉባቸው ሲሆን፣ ለአንዳንድ ጥሪዎች ምላሽ መስጠት የሚችል አጋር ማግኘታችን በጣም ተጋላጭ ለሆኑ የማኅበረሰባችን አባላት ሊያግዝ የሚችል ጠቃሚ ግብዓት ነው።"