U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

የሠራተኛ መረጃ ማጠቃለያ፦ የሕክምና ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክተር ሲሆኑ በAmerican Medical Association Network Open ጆርናል ላይም ጽሑፋቸው ታትሟል

ሰኞ ፣17 ማርች 2025
" ራስን ለማጥፋት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የሆኑ አዋቂዎችን ለመለየት የሚያስችል የአሠራር መዋቅርን መዘርጋት እና በተለይ ከእስር ለሚወጡ ግለሰቦች የሚቀርብ ማኅበረሰቡን መሠረት ያደረገ የልየታ እና የመከላከል ሥራ እንዲሠራ ጥናቱ ይመክራል። "
የCambridge Police Department የሕክምና ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት Dr. James Barrett፣ በቅርቡ በAmerican Medical Association (JAMA) Network Open ጆርናል ላይ ጥናቱን ያሳተመው የተመራማሪዎች ቡድን አባል ሆነው ሲሠሩ ቆይተዋል።

በቅርቡ ከእስር ከተፈቱ በኋላ ራሳቸውን ያጠፉ አዋቂዎች ብዛት የተሰኘው ጥናት United States ውስጥ ራሳቸውን በማጥፋት ከሚሞቱ 5 አዋቂዎች መካከል አንዱ ከሞታቸው በፊት ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ቢያንስ አንድ ምሽት እስር ቤት ቆይተው እንደነበር የሚያመላክት መረጃ አግኝቷል። ጥናቱ የተካሄደው ከብሔራዊ የአእምሮ ጤና ኢንስትቲውት(NIMH) የጤና እና ፍትሕ ውህደት ራስን ማጥፋት የመከላከያ ብሔራዊ ማዕከል (NCHATS) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው። Dr. Barrett እና የHealth Equity Research Lab ዳይሬክተር የሆኑት Dr. Ben Cook ማዕከሉ እያካሄደው ካለው አራት ዋና ዋና ፕሮጀክቶች ለአንዱ ተባባሪ ዋና መርማሪዎች ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።

ተመራማሪዎች ቀደም ሲል በእስር ላይ በነበሩ አዋቂዎች መካከል ያለውን የሞት ምጣኔ በተመለከተ ከ10 ጥናቶች የተገኘውን መረጃ አጠናቅረዋል። ተመራማሪዎቹ በጥናቱ እንዳገኙት US ውስጥ ከሚገኙ አዋቂዎች መካከል 20 በመቶ የሚጠጉት አዋቂዎች ራሳቸውን ያጠፉት ከእስር ከተፈቱ ባለው አንድ ዓመት ውስጥ ሲሆን፣ 7 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከእስር ከተለቀቁ ባለው ሁለተኛ ዓመት ውስጥ ነው። ራስን ለማጥፋት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የሆኑ አዋቂዎችን ለመለየት የሚያስችል የአሠራር መዋቅርን መዘርጋት እና በተለይ ከእስር ለሚወጡ ግለሰቦች የሚቀርብ ማኅበረሰቡን መሠረት ያደረገ የልየታ እና የመከላከል ሥራ እንዲሠራ ጥናቱ ይመክራል።

Dr. Barrett ከCambridge Police Department እና ከCambridge Health Alliance የHealth Equity Research Lab ጋር እየሠሩ ያሉት ሥራ የአእምሮ ጤና ችግሮች እያጋጠሟቸው ያሉ ግለሰቦችን ለመርዳት ያላቸውን ቁርጠኛ አቋም ያሳያል። CPD ውስጥ የሕክምና ድጋፍ ክፍሉን እየመሩ የሚገኙ ሲሆን፣ የክፍሉም ሠራተኞች የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች አላስፈላጊ እስርን እና ማስቆምን ለመከላከል በልዩ ሁኔታ ከሰለጠኑ የፖሊስ መኮንኖች ጋር አብረው እየሠሩ ይገኛሉ። የDr. Barrett ቡድን የጉዳይ አስተዳደር እና ክትትል አሠራር ዘዴ የሚጠቀም ሲሆን፣ ማኅበረሰቡ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ለሚያጋጥሟቸው የአእምሮ ጤና አደጋ ጥሪዎች የሚሆኑ ማኅበራዊ ጉዳይ ሠራተኞችን ተጠቅሞ የማረጋጋት እና የድጋፍ ሥራ ይሠራል። ከዚህም በተጨማሪ CPD ለአሁኑ ሞዴሉ እንደ ማሻሻያ የሚሆን የጋራ ምላሽ ሰጪ ሞዴልን ዘርግቷል። አንድ የሕክምና ባለሙያ እና አንድ የፖሊስ መኮንን አንድ የፖሊስ መኪና ውስጥ በመሆን፣ ወደ 911 የሚደረጉ ከአእምሮ ጤና ችግር ጋር ተያያዥ ለሆኑ የከተማ ጥሪዎች ምላሽ ይሰጣሉ።
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here