እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች እና ትብብሮች ከትምህርት ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ አገልግሎቶችን ለCambridge ቤተሰቦች ማስፋፋት ቀጥለዋል።
ሰኞ ፣17 ማርች 2025
"
ባለፉት ሁለት ዓመታት በ19 የDHSP ድህረ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራሞች 246 የክፍል ወንበሮች የተጨመሩ ሲሆን፣ ይህ ጭማሬም አቅርቦቱን በ20 በመቶ እንዲያድግ አድርጎታል።
"
Department of Human Service Programs ከትምህርት ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ አገልግሎቶች አማራጮችን ለCambridge ቤተሰቦች ለማስፋፋት ከአጋሮች ጋር እየሠራ ይበልጥ ፍትሐዊ የሆነ የማመልከቻ እና የምዝገባ ሂደት ለመፍጠር ቁርጠኛ ነው።
DHSP ከ2021 ዓ.ም ጀምሮ ለቤተሰቦች የተደራሽነት እንቅፋቶችን ለማስወገድ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ምዝገባን ለማሳደግ ከትምህርት ሰዓት በኋላ የሚሰጡ አገልግሎቶቹ ዙሪያ የሚደረጉ የማመልከቻ እና የምዝገባ ሂደቶች ላይ ለውጦችን አስተዋውቋል። መምሪያው ከKindergarten ጀምሮ እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ ላሉ የCambridge ልጆች ከትምህርት ሰዓት በኋላ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በሚከተሉት አራት ሞዴሎች ያቀርባል፦ Childcare Afterschool፣ Community Schools፣ King Open Extended Day እና Cambridge Youth ፕሮግራሞች። ሁሉም የፕሮግራም ሞዴሎች የልጆችን ማህበራዊ-ስሜታዊ ትምህርት የሚያዳብሩ ሲሆን፣ ይህንን ትምህርት ለመደገፍ በአዋቂዎች እና ልጆች መካከል አዎንታዊ ግንኙነቶችን ይጠቀማሉ። ለ2024-2025 ዓ.ም የትምህርት ዘመን 1,486 ተማሪዎች በDHSP ከትምህርት ሰዓት በኋላ የሚሰጥ አገልግሎት ፕሮግራም በኩል አገልግሎት የቀረበላቸው ሲሆን፣ ከእነዚህ አቅርቦቶች መካከል 90 በመቶው ቤተሰቡ አንደኛ ምርጫ ባደረጋቸው ምድቦች የቀረቡ ነበሩ። በተጨማሪም የሎተሪው ቅድሚያ የሚሰጣቸው የገቢ ደረጃ ቡድን ላይ በነበሩት አመልካቾች ዘንድ የ7 በመቶ ጭማሪ የታየ ሲሆን፣ ይህም በፕሮግራሞች ውስጥ ላይ ያለውን የዘር ብዝሃነት እያሳደገ ይገኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በ19 የDHSP ከትምህርት ሰዓት በኋላ የሚሰጥ አገልግሎት ፕሮግራሞች ላይ 246 መቀመጫዎች የተጨመሩ ሲሆን፣ ይህም በአቅርቦት ረገድ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ለ2024-2025 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ20 በመቶ ጭማሪ እንዲኖር አድርጓል። መምሪያው በከተማ አስተዳደሩ የገንዘብ ድጋፍ በማኅበረሰባዊ ከትምህርት ሰዓት በኋላ የሚሰጥ አገልግሎት ፕሮግራሞች ውስጥ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች 91 መቀመጫዎችን መጨመር ያስቻለ ድጋፍ አድርጓል። 2024 ዓ.ም ከትምህርት ቤት ሰዓት ውጪ የሚገኙ ልጆች አጀንዳ (AFCOST) የተሰኘው የDHSP እና Cambridge public schools ትብብር በDHSP እና በማኅበረሰባዊ ከትምህርት ሰዓት በኋላ የሚሰጥ አገልግሎት ፕሮግራሞች ላይ ቀጣይነት ያለው መረጋጋት እና እድገት እንዲኖር የሚያስችሉ ምክረ ሃሳቦችን ለመስጠት የOST ማስፋፊያ ጥናት ጀምሯል።
በተጨማሪም ከትምህርት ሰዓት በኋላ የሚሰጥ አገልግሎት ፕሮግራሞች እና ሂደቶች በጊዜ ሂደት ሲቀየሩ DHSP የእንክብካቤ ሰጪውን አስተያየት ማዕከላዊ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው። በ2024 ዓ.ም የተለያዩ የእንክብካቤ ሰጪ አመለካከቶችን በሚያቀርቡ 14 የCambridge ነዋሪዎች ለተዋቀረው የDHSP የእንክብካቤ ሰጪዎች ምክር ቤት 2ኛ ዑደት የተደረገውን ምልመላ ሠራተኞቹ ደግፈዋል። የእንክብካቤ ሰጪዎች ምክር ቤት ከትምህርት ሰዓት በኋላ የሚሰጥ አገልግሎት ዙሪያ የሚሰጡ ውሳኔዎችን በመረጃ ለመደገፍ፣ በተለምዶው ችላ የሚባሉ ድምጾችን ለማጉላት እና ፕሮግራሞችን እና ሂደቶችን በማሻሻል ረገድ የእንክብካቤ ሰጪዎችን ተሳትፎ ለማበረታታት በየጊዜው ከDHSP ሠራተኞች ጋር ይገናኛል።