መኖሪያ ቤት የሌላቸው የማኅበረሰብ አባላትን ለመደገፍ ለሚያገለግል አዲስ ግንዛቤ ማስጨበጫ ቫን የገንዘብ ድጋፍ ተገኝቷል
ሰኞ ፣17 ማርች 2025
"
ለአንዳንድ ጥሪዎች ምላሽ መስጠት የሚችል አጋር ማግኘታችን በጣም ተጋላጭ ለሆኑ የማኅበረሰባችን አባላት ሊያግዝ የሚችል ጠቃሚ ግብዓት ነው።
"
የከተማ አስተዳደሩ እና Bay Cove ሰብዓዊ አገልግሎቶች የቤት አልባ ነዋሪዎችን ፍላጎት በተሻለ መልኩ ለማሟላት ኖቬምበር ወር ላይ አዲስ የተጓዳኝ አገልግሎቶች ግንዛቤ ማስጨበጫ ቫን ይፋ አድርገዋል። ይህ የተሻሻለ የጎዳና ግንዛቤ ማስጨበጫ ቫን የሕክምና ምርመራዎች ለማድረግ፣ መለስተኛ ሕክምናዎችን ለመስጠት እና በጤና እንክብካቤ ባለሙያዎች እና ቤት አልባነትን እየተጋፈጡ በሚገኙ ሰዎች መካከል ስብሰባዎችን ለማስተባበር የሚያስችሉ መሳሪያዎችን የያዘ ነው። በተጨማሪም ቫኑ በCambridge Health Alliance Emergency Department (የCambridge የጤና ህብረት የአደጋ ጊዜ መምሪያ) ውስጥ የቤት አልባ ሰዎች መጠለያ ላይ በተመሰረቱ ክሊኒኮች በሚያገለግሉ ተዓማኒነት ያላቸው አገልግሎት አቅራቢዎች አማካኝነት የጤና ምርመራ እና ሕክምና በማቅረብ ለዚህ ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍል የሚደረገውን እንክብካቤ ቀጣይነት ይደግፋል።
ለግንዛቤ ማስጨበጫ ቫኑ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት የተቻለው የማኅበረሰብ ጤናን ለሚያሻሽሉ የከተማ አስተዳደር እና የcommonwealth ፕሮግራሞች የሚደረግ የድጎማ ገንዘብ ለማግኘት ማመልከቻ በሚያስገባው እና የገንዘብ ድጋፉን በሚያስተዳድረው Department of Human Service Programs (DHSP፣ የሰብዓዊ አገልግሎት ፕሮግራሞች መምሪያ) የዕቅድ አወጣጥ እና ልማት ክፍል ውስጥ ባሉት ሠራተኞች አመራር አማካኝነት ነው። በ2020 ዓ.ም የDHSP ሠራተኞች ከCity Manager’s Substance Use Advisory Committee (የCity Manager የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት አማካሪ ኮሚቴ) ጋር በቅርበት በመስራት ለቤት አልባ ማኅበረሰቦች የሚቀርቡ የጎዳና ሕክምና አገልግሎቶችን ለማሻሻል እና ለማስፋፋት የሚውለውን Opioid Settlement የተሰኘ የገንዘብ ድጋፍ ማስገኘት የቻሉ ሲሆን፣ ይህ ፕሮግራም የጀመረው በ2020 ዓ.ም የፌደራል የኮቪድ-19 የእፎይታ ድጎማ ገንዘብን በመጠቀም ነበር። የDHSP ሠራተኞች ለቫኑ የገንዘብ ድጋፍ ከተቀበሉ በኋላ የጤና እንክብካቤን የሚደግፉ መሳሪያዎችን ለመግዛት እና ቫኑ ላይ ለመግጠም ከDepartment of Public Works (የመንግሥታዊ ሥራዎች መምሪያ) ጋር በትብብር ሠርተዋል።
የDHSP የዕቅድ አወጣጥ እና ልማት ክፍል በተቀናጁ እና ማኅበረሰብ ተኮር በሆኑ ሂደቶች አማካኝነት ቤት አልባነትን ለመፍታት እየሠሩ በሚገኙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ቡድን የተዋቀረውን Cambridge Continuum of Care ይቆጣጠራል።