Cambridge Arts ከ280+ በላይ የሚሆኑ የሕዝብ የሥነ-ጥበብ ሥራዎችን እንዴት እንደሚንከባከብ ማሳያ
ሰኞ ፣17 ማርች 2025
የCambridge ከተማ አስተዳደር 1979 ዓ.ም ላይ በአከባቢው ተግባራዊ የሚሆን አንድ መቶኛ ለሥነ ጥበብ የተሰኘ ድንጋጌ ማጽደቁን ላያውቁ ይችላሉ። መንግሥት ከሚያወጣው በጀት ከ1 በመቶኛ ያላነሰው የግንባታ በጀት ለአካባቢው ተስማሚ በሆነ መልኩ ለሚሠሩ የሕዝብ ሥነ ጥበብ ሥራዎች እንዲመደብ የCambridge ድንጋጌ ያስገድዳል። ይህን የሕዝብ ሥነ ጥበብ ሥራ የመሥራት ቁርጠኝነት በድንጋጌ ካስቀመጡ፣ ለዚህም ሥራ የሚሆኑ ሠራተኞችን ከመደቡ የMassachusetts ጥቂት ማህበረሰቦች መካከል Cambridge አንዱ ነው። በመሆኑም በአካባቢው ከሚገኙ ዘመናዊ የሥነ ጥበብ ስብስቦች መካከል ትልቁ ስብስብ የሚገኘው Cambridge ውስጥ ነው፤ በመሆኑም ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጥበባትን ባሉበት ሁኔታ ጠብቆ የማቆየት ኃላፊነቶች አሉ።
ውጭ የሚገኙ የሕዝብ የሥነ ጥበብ ሥራዎች በጥንቃቄ በሙዚየሞች የሥነ ጥበብ አዳራሾች ውስጥ ከሚቀመጡት በተለየ መልኩ እንደ ዝገት፣ ማስቲካ፣ ፈሳሽ ቆሻሻዎች፣ ግራፊቲ፣ አውሎ ንፋሶች እና ከፋ ሲባል ደግሞ የገልባጭ መኪና አደጋዎች የመሳሰሉ መልከ ብዙ ተግዳሮቶች ያጋጥሟቸዋል።
“Rust Happen(s): Caring for the Public Art Collection" የተሰኘው ኤግዚቢሽን ማርች ወር 2024 ዓ.ም ላይ ይፋ የደረገ ሲሆን፣ Cambridge Arts እንዴት በአካባቢው ለሚገኙ የግድ ግዳ ላይ ምስሎች፣ ሞዛይኮች እና ሐውልቶች እንክብካቤ እንደሚያደርግ ያሳየ ነበር። ኤግዚቢሽኑም Konstantin Simun በIgor Fokin አሻንጉልት DooDoo የመዳብ መታሰቢያ ሐውልት ላይ ባለው የወርቅ ሽፋን በየዓመቱ የሚደረገውን ጠብቆ የማቆየት ሥራ መዝግቦ ያሳየ ሲሆን፣ ይህም ሐውልት የተሠራው Fokin 1996 ዓ.ም ላይ ከዚህች ዓለም በሞት ከመለየታቸው በፊት በየጊዜው ትዕይንት ያቀርቡበት በነበረ፣ Harvard Square ላይ በሚገኝ አንድ ቦታ ላይ ለFokin መታሰቢያነት እንዲሆን ታስቦ የተሠራ ሐውልት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ኤግዚብሽኑ እንዴት የVusumuzi Maduna “Inner City Totem I” የተሰኘው የጥበብ ሥራ ላይ የነበሩ፣ ለአራት አሥርት ዓመታት ያክል ውጪ በመቆየታቸው በስብሰው የነበሩ የእንጨት ምሰሶዎች እንደተቀየሩም አሳይቷል።
“Rust Happen(s)" የተሰኘው ሥራ የሥነ ጥበብ ጥበቃ ክፍል ዳይሬክተር በሆኑት Craig Uram የሚመራው የCambridge Arts ቡድኑ፣ እነዚህን የማኅበረሰብ ዕንቁ የሆኑ የሥነ ጥበብ ሥራዎች ለወደፊት ትውልድ ጠብቆ ለማቆየት የሚጠቀማቸውን ሳይንሶች፣ ክህሎቶች እና እየሠራ ያላቸውን ሥራዎች አሳይቷል። ለዚህ ሥራ የሚያገለግሉ ብሩሾች፣ ቀለም ማሟሚያዎች፣ የዋክስ እና ፓቲና መሣሪያዎች፣ የወርቅ ሽፋን መሥሪያ ድንኳኖች፣ መሰላሎች፣ መርፌዎች፣ ቫኪዩሞች፣ የአየር ግፊት ማጠቢያዎች፣ ግራፊቲ ማስለቀቂያዎች እንዲሁም በተፈጥሮ ኢንዛይሞች የሽንት ጠረን የሚያስወግዱ ንጥረ ነገሮችን ጨምሮ የተለያዩ መሣሪያዎች እዚህ ኤግዚቢሽን ላይ ቀርበዋል።
Cambridge Arts የከተማው ነዋሪዎች ወይም ጎብኚዎች በተጎዳ ወይም በጠፋ የሕዝብ ሥነ ጥበብ ሥራ ዙሪያ የሚሰጡትን ጥቆማ ለመስማት ሁሌም ዝግጁ እና ደስተኛ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ሰዎች የሚወዷቸውን የሕዝብ ሥነ ጥበብ ሥራዎች እይታንም ሲያጋሯቸው ደስ ይላቸዋል። የኤግዚብሽኑ ዓላማ የሥነ ጥበብ ሥራዎች ለሕዝብ በተዘጋጁ ቦታች ላይ እንዲኖሩ ማኅበረሰቡ በሚጫወተው ትልቅ ሚና ዙሪያ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራን መሥራት ነበር።