U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

የቅርብ ጊዜ ዜናዎችን እና ዋና ዋና ክስተቶችን ዞር ብለን እንቃኝ

ሰኞ ፣17 ማርች 2025
Picture of City Manager speaking at a ceremonial signing.
የCambridge City Manager Huang Cambridge በሚገኘው Ragon Institute ውስጥ የተዘጋጀውን የስቴቱን የ4 ቢልየን ዶላር የኢኮኖሚ ልማት አዋጅ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ታድመው ንግግር አድርገዋል።
" ይህ እኛ የምንኖርበት ማኅበረሰብ ብዙ ሥራዎችን ለመሥራት ተግቶ እየተንቀሳቀስ ያለ ማኅበረሰብ ነው። "
ከCity Manager የተሰጠ መልዕክት

የ2025 ዓ.ም ጉዟችንን በአግባቡ እየተጓዝን ነውና ይሄን አጋጣሚ ባሳለፍነው ዓመት በነበሩ ክስተቶች ዙሪያ አጭር ማጠቃለያዎችን ለመስጠት፣ መለስ ብለንም ያከናወናቸውን ሥራዎች ለማየት መጠቀም እሻለሁ። በ2024 ዓ.ም በጋራ ማሳካት በቻልነው ነገር ኩራት ይሰማኛል፤ Cambridge ከሌሎቹ የተለየ ማኅበረሰብ የሚገኝባት የተለየች ከተማ ነች።

በየዕለቱ ለእርስ በእርሳችን እንዴት እንደምንተሳሰብ እና የተሻለ ዓለም ለመፍጠር እንደምንሰራ ስመለከት እደነቃለሁ። ፈታኝ፣ አወዛጋቢ እና በጥርጣሬ የተሞላ ወደሚሆን ጊዜ እየተሸጋገርን እንደመሆኑ መጠን የአካባቢ መስተዳድራችን ጠንካራ፣ እሴቶቻችንን ለመከላከል የተዘጋጀ እና በCambridge ውስጥ ለሚኖር፣ ለሚሠራ እና ለሚጫወት ሰው ሁሉ የተሻለ ማኅበረሰብ ለመገንባት ቁርጠኛ የሆነ በመሆኑ አመስጋኝ ነኝ።

እጅግ በጣም ብዙ ሥራ በመሥራት ላይ የሚገኝ ማኅበረሰብ አለን። በከተማው ምክር ቤት በዘላቂነት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተብለው የቆዩ ሁለት ዋነኛ ተነሳሽነቶች ባለፈው ዓመት ተጀምረዋል። በመጀመሪያ በCambridge ለሚገኝ እያንዳንዱ የአራት ዓመት ህፃን እና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የሶስት ዓመት ህፃናት በመደበኛ የትምህርት ሰዓት እና ወቅት የሚሰጥ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ወጪዎችን ለመሸፈን የሚረዳ ገንዘብ ድጋፍ የሚያቀርብ የCambridge Preschool ፕሮግራም (CPP) አስጀምረናል። እንዲሁም በድንገተኛ አደጋዎች ጊዜ ለሚደረጉ የ911 ጥሪዎች አማራጭ ሆኖ የሚያገለግል የማኅበረሰብ ድጋፍ ምላሽ እና ተሳትፎ (CARE) የተሰኘ ያልታጠቀ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጪ ቡድን አቋቁመናል። በዚህ የዜና መጽሔት ውስጥ አለፍ ብለው ስለ CARE ተጨማሪ ማንበብ ይችላሉ።

የምክር ቤቱን እና የማኅበረሰቡን ግቦች እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች የሚያንፀባርቅ በጀት መቅረጽ በመቻላችን ኩራት ይሰማኛል። ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መኖሪያ ቤቶች ላይ $47 ሚሊዮን፣ የመኖሪያ ቤት እጦት እና የመኖሪያ ቤት አቅርቦት አለመረጋጋትን ለመፍታት የሚሠሩ ተነሳሽነቶች ላይ $16 ሚሊዮን፣ ሁሉን አቀፍ ቅድመ-መዋዕለ ህፃናት ትምህርትን ለማስፋፋት $34 ሚሊዮን፣ በአየር ንብረት Net Zero (ምንም አይነት በካይ ልቀት የማያመነጭ) የመሆን ግባችንን ለማሳካት $17 ሚሊዮን እና ለVision Zero እና የትራፊክ ደኅንነት ደግሞ $13 ሚሊዮን ኢንቬስት እናደርጋለን። Cambridge Public Schools $270 ሚሊዮን ዶላይ በመውሰድ ከበጀታችን ትልቁን ድርሻ የሚይዝ ሲሆን፣ ለረጅም ጊዜ በትምህርት ቤት ኮሚቴው ቅድሚያ ተሰጥቶ ሲሠራበት የነበረውን ረዘም ያለ የትምህርት ቀን በመደገፍ ጭምር በዚህ ዓመት የመምህራን ደሞዝ ላይ ከፍተኛ ጭማሪዎች አድርገናል። ባሳለፍናቸው ዓመታት ከምክር ቤቱ ጋር በመተባበር ለተቋቋሙት የተለያዩ ወሳኝ ፕሮግራሞች ድጋፍ እያደረግን እንቀጥላለን፦ ለቤት አልባ ሰዎች የሚሆኑ አገልግሎቶች እና ድጋፍ፣ የሥራ ስልጠና እና ቀጣይነት ያላቸው የትምህርት ፕሮግራሞች፣ ነዋሪዎችን እና አነስተኛ የንግድ ሥራዎችን ለማገልገል እየተስፋፋ የሚገኘው የከተማ ብስባሽን ዳግም ጥቅም ላይ የማዋል ሥራ፣ በየዓመቱ ከ1,000 በላይ ዛፎችን በመትከል ላይ የሚገኘው የከተማ ደን ልማት ክፍል እና ሌሎችም ይገኙበታል።

እኔ በዋነኝነት ቅድሚያ የምሰጠው ነገር ግልጸኝነትን እና ተጠያቂነትን ማስፈን ነው። Cambridge ውስጥ እጅግ በጣም ከፍተኛ የጥራት ደረጃ እንጠብቃለን። በቅርቡ የCity Manager የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሂደናል፤ ይህም ሥራውን ስይዝ ተጠያቂነትን ለማስፈን የገባሁት ወሳኝ ቃልኪዳን አካል ሲሆን፣ በከተማ አስተዳደር ደረጃም ሲከናወን ሁለተኛ ዓመቱ ነው። በታላላቅ ግቦቻችን ላይ፣ ስኬት ያገኘንባቸው ቦታዎች ዙሪያ እና ማሻሻል የሚኖርብን አካባቢዎችን አስመልክቶ መለስ ብሎ ለመዳሰስ ዕድሉን በማግኘቴ በድጋሚ አመሰግናለሁ።

መርሃ ግብሬ በምክር ቤት ስብሰባዎች (በ2024 ዓ.ም መጨረሻ 38 ነበሩ)፣ የኮሚቴ ችሎቶች፣ የማኅበረሰብ ዝግጅቶች፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎች እና በመቶዎች በሚቆጠሩ የአንድ ለአንድ ንግግሮች እና ምናባዊ መግለጫዎች የተጨናነቀ ነበር። እነዚህ ጥልቅ ውይይቶች በአሠራሮቻችን ረገድ ይበልጥ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ መስጠት እንድንችል እና የማኅበረሰባችንን ልዩ ፍላጎቶች እና ምኞቶች ታሳቢ ባደረገ መልኩ አገልግሎቶችን እንድናሻሽል ረድተውናል። ይህ ጥረት 2025 ዓ.ም ላይ ሲስፋፋ ለማየት ጓጉቻለሁ።

Cambridge የምትመራው የተሻለ ማኅበረሰብ ለመገንባት በየዕለቱ ተግተው እየሠሩ የሚገኙ አስደናቂ መሪዎች እና ሠራተኞችን በያዘ ቡድን ሲሆን፣ የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች ከሚጠበቅባቸው በላይ በመሄድ የሰሩትን ሥራ የሚዘክር ታሪክም በየጊዜው እሰማለሁ። በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚገኙት አጋሮቻችን የዜግነት ትስስራችንን የሚያጠናክሩ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች፣ የንግድ ሥራዎች እና የመብት ተሟጋች ቡድኖችን በማቋቋም አስደናቂ ስራ እየሰሩ ነው። ነዋሪዎቻችን በቦታው ይገኛሉ፣ ግብረመልስ ይሰጣሉ እንዲሁም በአካባቢ መስተዳድር ውስጥ ይሳተፋሉ። የከተማው ምክር ቤት በመላው Commonwealth ውስጥ በሚገባ ማኅበረሰባቸውን የሚወክሉ፣ ግልጽ የሆኑ እና ተጠያቂነት የሰፈነባቸው ከሚባሉት የተመረጡ የአስተዳደር አካላት ዘንድ ተምሳሌት መሆኑን ቀጥሏል።

በዚህ ውብ ማኅበረሰብ ውስጥ ትርጉም ያለው ተጽዕኖ ለመፍጠር ስፍር ቁጥር የሌላቸው ዕድሎች የምናገኝበትን መጪው ቀጣይ ዓመት ለመቀበል በጉጉት እጠባበቃለሁ። ለማገልገል ዕድል ስለሰጣችሁኝ፣ ወደፊትም አብረን ለምሠራው ሥራ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። 

መልካሙን ሁሉ እየተመኘሁ፣ ቀሪው 2025 ዓ.ም ግሩም ይሁንልዎ ስል ያለኝን መልካም ምኞት መግልጽ እወዳለሁ!

Yi-An Huang፣ City Manager
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here