በቅርቡ አንድ Cambridge ውስጥ የሚሠራ እና የሚኖር ቤተሰብ “ህልም እውን ሆኗል”። ከተማው ለመጀመሪያ ጊዜ ቤት ገዢዎች ካዘጋጃቸው ፕሮግራሞች አንዱ በሆነው HomeBridge አማካኝነት የቤት ባለቤቶች ሆነዋል። አዲሱ የቤት ባለቤት “Cambridge ቤት እገዛለሁ ብዬ አልጠበኩም ነበር። የከተማ አስተዳደሩ ይህን ትልቅ ሚና ባይጫወት ኖሮ፣ ተመጣጣኝ የይዞታ ዋጋ ወደሚገኝባቸው ሌሎች አካባቢዎች መሄድ ይኖርብኝ ነበር" ሲሉ ተናግረዋል።
በተለየ ሁኔታ Cambridge ውስጥ የሚገኘው የዚህ ቤት ሽያጭ “ህልም እውን ማድረጉ” ብቻም ሳይሆን፣ በCambridge HomeBridge ፕሮግራም አማካኝነት ታግዞ የተደረገ 100ኛ የቤት ግዢ መሆኑም የፕሮግራሙ ወሳኝ ምዕራፍ ያደርገዋል። HomeBridge Cambridge ውስጥ የሚገኙ ገቢያቸው ከዝቅተኛው የገቢ መጠን ከፍ የሚሉ እና በመካከለኛው የገቢ መጠን እርከን ውስጥ የሚገኙ፣ ብቁ የቤት ገዢዎችን የሚያግዝ በከተማው ድጋፍ የሚያገኝ ፕሮግራም ነው። ፕሮግራሙ በክፍት ገበያ ቤት ለመግዛት የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣል። በምትኩም ቤት ገዢዎቹ የሚገዙት ቤት የከተማ አስተዳደሩ የተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤቶች ክምችት መዝገብ ላይ በቋሚነት እንዲጠቀሱ የሚያደርግ ስምምነት ይገባሉ (ገደብ ይጣልባቸዋል)።
"ይህ መልካም አጋጣሚ ለእኛ ትልቅ ቦታ ያለው ሲሆን፣ ትልቅ ስኬትም ነው" ሲሉ የቤቱ ባለቤት ተናግረዋል። "ያቀድነው ነገር አይደለም። የሆነ የሃሳብ ምድረ በዳ የሚመስል ቦታ ላይ ነበርን። አሁን ላይ ግን ከተማ አስተዳደሩ የወጪውን ከፍተኛ ድርሻ ሸፍኖልን የቤት ባለቤት በመሆናችን ከፍተኛ አድናቆት እና ታላቅ የምስጋና ስሜት ተሰምቶናል።
HomeBridge በተመጣጣኝ ዋጋ የመኖሪያ ቤት አማራጮች በማይገኙባቸው ሰፈሮች ላይ በቋሚነት ተመጣጣኝ የሆኑ አዲስ የቤት ባለቤትነት አማራጮችን አንድ በአንድ በመፍጠሩ በዓይነቱ ልዩ ያስብለዋል።
የCambridge ቤቶች ዳይሬክተር Chris Cotter እንደሚሉት “HomeBridge አንድ ቤተሰብ ባለው እና ገበያው በሚጠይቀው የመግዛት አቅም መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ይሠራል። የገበያው ሁኔታዎች ግን አሁንም አሉ።
ይህ ፕሮግራም ግን ቤተሰቦች ወደ ገበያው እንዲገቡ የሚያስችላቸው ሲሆን፣ በጊዜ ሂደትም በከተማው ውስጥ ተመጣጣኝ ቤቶችን እንድንፈጥር ይረዳናል። በተለይ ደግሞ ቤተሰብን ያማከሉ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን መኖሪያ ቤቶች መፍጠር ችለናል።"
ስለ HomeBridge ተጨማሪ ለማወቅ https://www.cambridgema.gov/HomeBridge ድረ-ገጽን ይጎብኙ።