U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

2024 ዓ.ም ላይ Cambridge ውስጥ በብዛት የተነበቡ መጻሕፍት

ሰኞ ፣17 ማርች 2025
የCambridge Public Library 2024 ዓ.ም ላይ ላይብረሪ በሚመጡ ተጠቃሚዎች በተውሶ ከተወሰዱ መጻሕፍት ከፍተኛ ቦታዎች የያዙ 10 የመጽሐፍ ርዕሶችን በዘርፍ እና በእትም ዓይነት ይፋ አድርጓል። 2024 ዓ.ም ላይ Cambridge ውስጥ የተነበቡትን መጻሕፍት እነሆ፦
የCambridge Public Library በሚገኝባቸው ሁሉም ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ቦታውን የያዘው የልብ ወለድ መጽሐፍ ሲሆን፣ የJames McBride “The Heaven & Earth Grocery Store” የተሰኘው መጽሐፍ ከ660 በላይ የሚሆኑ ጠቅላላ ተውሶዎችን በማስመዝገብ ከፍተኛው ቦታ ይዟል። ከዚህም በተጨማሪ የKristin Hannah “The Women”፣ የDaniel Mason “North Woods” እና የPercival Everett “James” የተሰኙት መጽሐፎችም ከ500 በላይ ተውሶዎችን በማስመዝገብ ከፍተኛ የተወዳጅነት ቦታውን ይዘዋል። የJonathan Haidt “The Anxious Generation” የተሰኘው መጽሐፍ ከፍተኛውን የተወዳጅነት ቦታ በኢ-ልብወለድ ዘርፉ ሲይዝ፣ “Dog Man: The Scarlett Shedder” የተሰኘው የDav Pilkey መጽሐፍ ደግሞ በልጆች መጽሐፍ ዘርፉ ከፍተኛውን ቦታ ይዟል።

ቀዝቃዛው የክረምት የአየር ሁኔታ ለንባብ እና አንባቢያን ቁጥር መጨመር አስተዋጽዎ ያደርጋል? እንግዲያው ከፍተኛው የመጽሐፍ ተውሶ መጠን የነበረው ማርች ወር ላይ ነበር። 2024 ዓ.ም ላይ ከነበሩት 1.1 ሚሊዮን የመጽሐፍ ተውሶዎች ወደ 70,000 የሚጠጉት የተካሄዱት ማርች ወር ላይ ነበር።

በአጠቃላይ የCambridge Public Library ሁሉንም ለመቀበል፣ አእምሮን ለማነቃቃት እና ማኅበረሰቡን ለማጎልበት ከሰነቀው ተልእኮ ጋር የሚራመዱ ፕሮግራሞችን እና አገልግሎታችን በዚህ ዓመት በተሳካ ሁኔታ አቅርቧል። ከ963,000 በላይ ጎብኝዎችን ተቀብለናል፣ 3,918 ሕዝባዊ ፕሮግራሞችን አዘጋጅተናል፣ 1.8 ሚሊዮን መገልገያ እቃዎችን በሰባት ቤተ-መጻሕፍቶቻችን አሠራጭተናል። ይህ ዓመት በValente ቅርንጫፍ ውስጥ የሰመር የእሁድ ሰዓቶችን ያቀረብንበት ሁለተኛ ዓመት ሲሆን፣ በሌሎች ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችንም ላይ የአገልግሎት ሰዓት ጭማሪ የተደረገባቸው የመጀሪያው ሙሉ የሥራ ዓመት ነበር። ስለእነዚህ የአገልግሎት ሰዓት ጭማሪዎች ብዙ አዎንታዊ አስተያየቶች ተቀብለናል። STEAM at the Library የተሰኘው ፕሮግራማችን ለአራተኛ ዓመት ለተጠቃሚዎች አገልግሎት በማቅረብ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በፕሮግራሞቹ ያስተናገደ ሲሆን፣ ተጨማሪ የተውሶ የቴክኖሎጂ ምርት አቅርቦቶች እና የከተማ አስተዳደር ትብብሮች በማዘጋጀትም የዲጂታል እኩልነት ሥራችንን አስፋፍተናል። በአጠቃላይ 2088 ሰዎች ተሳታፊ ያደረጉ 104 ፕሮግራሞችን ለአረጋዊያን በማዘጋጀት አገልግሎት ሰጥተናል። 46,259 ሰዎችን ተሳታፊ ያደረጉ 1760 የሚሆኑ ፕሮግራሞችን ለሕፃናት እና በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ ለሚገኙ ልጆች ያዘጋጀን ሲሆን፣ ከCambridge Public Schools ጋር ባለን ቀጣይነት ያለው አጋርነት አማካኝነት 388 አዲስ የቤተ መጻሕፍት ካርዶችን ለአፀደ ሕፃናት ተማሪዎች መፈጠር ችለናል።
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here