በዕድሜ ለገፉ አዋቂዎች የሚሆኑ አዳዲስ የፕሮግራም ስንድቶችን አሁን ላይ ማግኘት ይቻላል
ሰኞ ፣17 ማርች 2025
የCambridge Council on Aging and Public Health Department (CPHD፣ የእርጅና እና የሕዝብ ጤና መምሪያ የCambridge ምክር ቤት) ሁልጊዜ ማኅበረሰባችን ውስጥ ለሚኖሩ በዕድሜ የገፉ አዋቂዎች ጤና እና ደኅንነት ትኩረት እንሰጣለን። የከተማው ሠራተኞች ይህንን በመደገፍ ዕድሜያቸው ከ60+ በላይ ለሆኑ አዋቂዎች በተለየ መልኩ የተዘጋጁ የሙዚቃ ዝግጅቶችን እና የምግብ ማብሰል ትምህርቶችን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶች በዚህ ዓመት አቅርበዋል።
የሃውስ ሙዚቃ ባንድ የሆነው Bobby Tynes and Friends በየወሩ ወደ Senior Center (የአረጋዊያን ማዕከል) በመምጣት ደማቅ የሙዚቃ ዝግጅት ሲያቀርብ ቆይቷል። ባንዱ በቋሚነት ይመጣ የነበረ ሲሆን፣ ተጋብዥ የሙዚቃ እንግዳዎቹ እና ታዳሚዎቹ ግን በየወሩ ይቀያየራሉ። እነዚህ ክፍለ-ጊዜዎች በዕድሜ የገፉ አዋቂዎች ከማኅበረሰቡ አባላት ጋር እንዲገናኙ፣ እና ፈጠራን በሚያነቃቁ እና እንዲንቀሳቀሱ በሚያደርጉ የሙዚቃ እና ዳንስ ዝግጅቶች ላይ እንዲሳተፉ እድል ሰጥተዋል። ነዋሪዎች የሙዚቃ መሣሪያዎቻቸውን አምጥተው እንዲቀላቀሉ፣ አብረው በአንድ ላይ እንዲዘፍኑ፣ እንዲደንሱ ወይም ደግሞ ዝግጅቱን በመታደም እንዲዝናኑ ተጋብዘው ነበር።
በሙዚቃ ዝግጅቶቹ ዙሪያ የተሰጡት አስተያየቶች በጣም አዎንታዊ (መልካም) ነበሩ። ተሳታፊዎቹ እነዚህ ዝግጅቶች ላይ በመገኘታቸው ከማኅበረሰባቸው ጋር ይበልጥ እንዲቀራረቡ፣ ስሜታቸው እና ጤናቸው እንዲሻሻል እና ስለ Cambridge Public Health Department (Cambridge የሕዝብ ጤና መምሪያ) የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እንዳደረገ ተናግረዋል። “ይህ ስፍራ ሞቅ ያለ፣ ወዳጅነት የሞላው ስፍራ ነው…ሙዚቃው ደግሞ ወደር የለውም” ሲል አንድ የማኅበረሰቡ አባል ተናግሯል። ሌላ ተሳታፊ ደግሞ “ሁሉንም ነገር እጅግ ወድጄዋለሁ!” ብለው ጠቅለል አድርገው መልዕክታቸውን ተናግረዋል።
ተሳታፊ መሆን ይሻሉ? ማርች ወር 2025 ዓ.ም ላይ ሊጀመሩ ስለታቀዱት የ2025 የሙዚቃ ዝግጅት ክፍለ ጊዜዎች ተጨማሪ መረጃ ያግኙ።
ምግብ ማብሰል ከሆነ ፍላጎትዎ CPHD ከEast End House (EEH) ጋር በመተባበር የሚሠራውን ሥራ ይከታተሉ። በዚህ ዓመት CPHD ከEEH ጋር በመተባበር በአመጋገብ እና ምግብ ማብሰል ዙሪያ ያውጠነጠኑ ዝግጅቶችን ለመጀመሪያ ጊዜ አቅርቧል። የከተማው ሠርራተኞች የምግብ አዘገጃጀት ማሳያዎችን ያቀርቡ ሲሆን፣ በአንዱ ማሳያ ላይ የተጋገረ ነጭ ባቄላ ፓስታ፣ የስኳር ድንች እና የዶሮ ሙሌቶች አዘገጃጀትን እና ለበዓል ዝግጅቱ ደግሞ የተጋገረ ፒር አዘገጃጀትን አሳይተዋል! ከዚህም በተጨማሪ የምግብ ማብሰል ወርክሾፖችንም አቅርበዋል። የምግብ ማብሰል ወርክሾፖቹ የተካሄዱት Foundry’s Food Lab ውስጥ ነበር። እያንዳንዱ ወርክሾፕ ተሳታፊዎች EEH ጓዳ ውስጥ ሊያገኟቸው የሚችሏቸውን ግብዓቶች በመጠቀም የተዘጋጁ፣ ለመከተል ቀላል እንዲሆን ተደርገው የተዘጋጁ ሁለት የምግብ አዘገጃጀት መመሪያዎችን ያካተተ ነበር። የCPHD ሠራተኞች የምግብ አዘገጃጀት መመሪያዎችን በተግባር ያሳዩ ሲሆን፣ እግረ መንገዳቸውን የአመጋገብ እና የጤና ርዕሶችንም ዳስሰው ነበር። ምግቦቹ ከተዘጋጁ በኋላ ክፍሉ በአንድ ላይ ተመግቦ ተደስተውባቸዋል። ተግባራዊነትን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ወርክሾፖቹ የተሳታፊዎችን የምግብ ምርጫዎች፣ የሥነ-ምግብ ርዕሶች ፍላጎት፣ በቤት ውስጥ ያለውን የመሣሪያ አቅርቦት እና የቤተሰብ ብዛት ከግምት ውስጥ ያስገቡ ነበሩ።
Cambridge ውስጥ በዕድሜ ለገፉ አዋቂዎች ተደራሽ የሆኑ ፕሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን ለማግኘት የCouncil On Aging ድር-ገጹን ይመልከቱ፦ www.cambridgema.gov/CouncilonAging።
"
አዲስ የተዘጋጁት ክፍለ ጊዜዎች በዕድሜ የጉፉ የማኅበረሰባችን አባላት መገናኘት የሚችሉባቸውን፣ በሙዚቃ እና በዳንስ ዝግጅቶችም ላይ የሚሳተፉባቸውን ዕድሎች መፍጠር ችለዋል።
"