የሠራተኛ መረጃ ማጠቃለያ፦ የፖሊስ መኮንኖች በHarvard and Central Square ግንኙነቶችን እየገነቡ የሚገኙ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ የCambridge Police ስትራቴጂ ትልቅ አካል ነው
ሰኞ ፣17 ማርች 2025
Cambridge ውስጥ የሚገኙት Harvard and Central Squares የራሳቸው የሆነ የተለየ ጠባይ ያላቸው ሲሆን፣ የCambridge Police Harvard Square/Central Square ቡድንም ይሄንኑ ጠባይ ለረዥም ጊዜ ሲያጠና ቆይቷል። ሳጅን Sean Lowe እና የፖሊስ መኮንን Joe Grassi በዋናነት የሚሠሩት በHarvard Square ቡድኑ ውስጥ ሲሆን፣ የፖሊስ መኮንኖች Frank Gutoski እና Billy Simmons ደግሞ Central Square ቡድኑ ውስጥ እየሠሩ ይገኛሉ። እነዚህ የፖሊስ መኮንኖች አደባባዮቹ ላይ ከሚገኙ የንግድ ሥራዎች፣ ነዋሪዎች እና ማኅበራት ጋር በቅርበት በመሥራት ችግሮችን ለመለየት እና ለመፍታት እንዲሠሩ ተሰማርተው ይገኛሉ። ሳጅን Lowe “በአካባቢው ባሉ የንግድ ስፍራዎች የምናውቃቸው ፊቶች መኖራቸው በጣም አስፈላጊ ነው” ብለዋል። “የሚያሹትን እንዲያገኙ የሚያስችል፣ እኛም ማቅረብ የምንችለውን እንድናቀርብ እና በሂደቱም እንድናግዛቸው መተማመን መኖሩ እግጅ አስፈላጊ ነው” ሲሉም የፖሊስ መኮንን Grassi አብራርተዋል።
Denise Jillson የHarvard Square Business Association ዋና ዳይሬክተር ናቸው። እንደሚሉትም ከሆነ የአከባቢው ሕዝብ ከCPD ጋር ባለው ትብብር እና አጋርነት እጅጉን ተጠቃሚ ነው። “ይህን ማኅበረሰብ አንድ አድርጎ በሰላማ ከሚያቆዩት አካላት መካከል ዋናኛዎቹ ናቸው” ሲሉ Jillson ተናግረዋል። "ከማኅበረሰቡ ጋር የሚደረጉት ግንኙነቶች ሙያዊ ሥነ ምግባር የተሞላባቸው፣ ተግባቢነትን እና ውጤታማነትን የሚያንጸባርቁ ናቸው። “የምናገኛቸው መረጃዎች እና አስተያየቶች የፖሊስ መኮንኖቹን የሚያውቁ የንግድ ሥራ ባለቤቶች እና ነዋሪዎች ሲኖሩ ግልጽ ግንኙነቶች እንዲፈጠሩ እና ጠንካራ እምነት እንዲዳብር የሚያግዝ መሆኑን ይነግሩናል” ሲሉ ሳጅን Lowe ተናግረዋል።
ይህ የምንሠራው ሥራ በሙሉ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ደማቅ ከተማ ለመፍጠር ታላሚ ያደረገ ነው።