U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

የSummer Food ፕሮግራም ለCambridge ወጣቶች ከ80,000+ በላይ ማዕዶችን አቅርቧል

ሐሙስ ፣13 ፌብሩወሪ 2025
የከተማው አስተዳደሩ በተለይ ደግሞ የትምህርት ክፍለ ጊዜ በማይኖሩባቸው በሰመር (በጋ) ወራት ላይ ለምግብ ዋስትና እጦት እና ጤና ቅድሚያ ይሰጣል። በDepartment of Human Service Programs ሥር የሚንቀሳቀሰው የCambridge Summer Food ፕሮግራም ሊኖሩ የሚችሉ ክፍተቶችን የሚሸፍንበት ቦታ እዚህ ላይ ነው። ግቡ ቀላል ነው፦ የCambridge ታዳጊዎች በሰመር ወራት ጤናማ ምግቦች ማግኘት መቻላቸውን ማረጋገጥ። በፕሮግራሙ አማካኝነት በሰመር ወቅት በዕድሜያቸው 18 ዓመት እና ከዚያ በታች ለሆኑ የCambridge ታዳጊዎች እያንዳንዱ የሥራ ቀን ላይ ነፃ እና በአስፈላጊ ንጥረ ነገሮች የተሞሉ ማዕዶችን ይቀርባሉ።

የዚህ ሥራ ስፋት ቀላል የሚባል አይደለም። ከጁላይ 1 እስከ ኦገስት 30 ቀን 2024 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ Summer Food ፕሮግራም ለCambridge ታዳጊዎች ከ80,000 በላይ ማዕዶችን አቅርቧል። ይህም በመላ ከተማው በሚገኙ ዘጠኝ መናፈሻዎች የቀረቡ 74,350 ነፃ የቁርስ እና የምሳ ማዕዶችን እንዲሁም መዝናኛ ክፍሉ በሚያዘጋጀው የወጣቶች ቅርጫት ኳስ እና የወጣቶች የጎዳና ሆኪ ሊጎች በሚዘጋጁባቸው ቦታዎች የቀረቡ 5,749 ነፃ የእራት ማዕዶችን ያካትታል። ፕሮግራሙ ለ40 በአካባቢው የሚገኙ የሰመር ካምፖች በነፃ የምሳ ማዕዶችን ያቀረበ ሲሆን፣ በ"Screen on the Green" የቤተሰብ ፊልም ምሽቶች ላይ ለተገኙ የማኅበረሰብ አባላት ደግሞ ነፃ ቁርሳ ቁርሶችን ሰጥቷል።

ከጤናማ ማዕዶች በተጨማሪ ፕሮግራሙ የተለያዩ መዝናኛ እንቅስቃሴዎችን ያቀርባል። የቁርስ እና የምሳ ማዕዶች እስኪቀርቡ ድረስ ታዳጊዎቹ በፓርኮቹ ለሚደረጉ ጨዋታዎች እና መዝናኛዎች የመዝናኛ ሠራተኞችን መቀላቀል ይችላሉ። በተጨማሪም ፕሮግራሙ በሕፃናት የንባብ ተነሳሽነት አጀንዳ፣ Center for Families እና Cambridge Public Library (የCambridge የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት) ትብብር የሚካሄደውን Cambridge Book Bike በSummer Food የማዕድ ጣቢያ በየሳምንቱ ያስተናግዳል። በCambridge Book Bike አማካኝነት ልጆች የተረት ተረት ጊዜ እና በነፃ የሚቀርቡ መጻሕፍትን ያገኛሉ።
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here