U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

Participatory Budgeting

Participatory Budgeting (PB) ዑደት 11

በኦንላይን እዚህ ድምጽ ይስጡ

Cambridge ከተማ አስተዳደር ሁሉንም 6 ክፍል ተማሪዎችን ጨምሮ ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ነዋሪዎች በከተማዋ ማሻሻያ ፕሮጀክቶች ላይ ድምጽ እንዲሰጡ ይጋብዛል። ይህ የምርጫ ሂደት U.S. ዜጋ ያልሆኑትን ሰዎች እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጨምሮ ለሁሉም Cambridge ነዋሪዎች ክፍት ነው። ድምጽ መስጠት የሚቻልበት የመጨረሻው ቀን ማርች 16 ቀን 2025 . ነው።

በኦንላይን የሚሰጥ ድምጽ በጽሑፍ መልእክት ወይም በኢሜይል በሚላክ ኮድ አማካኝነት ትክክለኛነቱ ይረጋገጣል። የኦንላይን ድምጽ መስጫው በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ፣ በአረብኛ፣ በባንግላ፣ በቻይንኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በጃፓንኛ፣ በሄይቲ ክሪኦል፣ በሕንድኛ፣ በስፔንኛ እና በፖርቱጋልኛ ይገኛል።

ድምጽ እንዲሰጥባቸው ለምርጫ የቀረቡትን የተለያዩ ፕሮጀክቶች መግለጫ ከታች መመልከት ይችላሉ።

የማህበረሰብ ሀብቶች

የሕፃናት ቁሳቁሶችን የያዙ ለአዲስ ወላጆች የሚሆኑ የእንኳን ደስ ያለዎት ሳጥኖች (ጥቅሎች) ($60,000)

ቦታ: በቤተሰቦች ማዕከል በኩል በከተማ አቀፍ ደረጃ እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።

አዲስ ወላጆችን እንደግፍ! የሕፃናት ቁሳቁሶች ውድ ናቸው፤ አዲስ ለተወለደ ሕፃን እንክብካቤ መስጠትም ከባድ ነው። ይህ የፕሮጀክት ሃሳብ ለአዳዲስ ወላጆች የሕፃናት ቁሳቁሶችን የሚያቀርብ ሲሆን፣ ወላጅ ወደመሆን በቀላሉ እንዲሸጋገሩ በሚያግዙ የማኅበረሰቡ ሀብቶች ዙሪያም ወላጆቹ መረጃ እንዲያገኙ ያደርጋል። 

Baby box with baby supplies for a new parent household 
በሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በነፃ የሚታደል ቅጫም ማስለቀቂያ ማበጠሪያዎች ($60,000)

ቦታ: በሁሉም የCambridge የሕዝብ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች።

የቅጫም ወረርሺኞች በሚከሰቱ ጊዜ ተጠቂ ቤተሰቦች የሚያወጡትን ወጪ ለማቃለል ታስቦ በነፃ የሚታደሉ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ቅጫም ማስለቀቂያ ማበጠሪያዎች። እነዚህ ማበጠሪያዎች ቅጫም ለማስለቀቅ በሚደረገው የእጥበት ሕክምና ወቅት ከመደበኛዎቹ ማበጠሪያዎች ይልቅ እጅግ ውጤታማ እንዲሆኑ በሚያደርግ መልኩ ጥቅጥቅ ተደርገው የተሠሩ ናቸው።
 Professional-quality lice comb
የከተማ ስብሰባዎች የቀጥታ ስርጭት የጽሑፍ መግለጫ ተደራሽነት ($250,000)

ቦታ: በከተማ አስተዳደሩ በባለቤትነት በተያዙ ሕንፃዎች እና በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ላይ እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።

በከፊልም ሆነ በሙሉ መስማት ለተሳናቸው ሰዎች የሕዝብ ስብሰባዎችን ይበልጥ ተደራሽ እና ለመታደም ምቹ እንዲሆንላቸው እናድርግ! ይህ የፕሮጀክት ሃሳብ በከተማ አስተዳደሩ በባለቤትነት በተያዙ ሕንፃዎች ውስጥ የሚካሄዱ የሕዝብ ስብሰባዎችን በቀጥታ ስርጭት የጽሑፍ ግልባጭ ለማዘጋጀት የሚሆኑ ተንቀሳቃሽ ስክሪኖችን እና የሰው ኃይልን ለማቅረብ ድጋፍ ያደርጋል።
 Live captioning in Sullivan Chamber
ተንቀሳቃሽ የቤት እንስሳ እንክብካቤ አገልግሎት ($200,000)

ቦታ: ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው መኖሪያ ቤቶች፣ በአረጋዊያን መኖሪያ ተቋማት እና በሌሎች ቦታዎች እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።

የገንዘብ ወይም እንቅስቃሴ ከማድረግ ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮች ላሉባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የእንስሳት ሕክምና ተደራሽነትን የማሻሻል ሥራ ይሠራል። ይህ የፕሮጀክት ሃሳብ ነፃ የሕክምና ክትትል፣ የክትባት ክሊኒኮች፣ የንጽሕና እና ውበት መጠበቂያ፣ የጥርስ ሕክምና እና ሌሎች አገልግሎቶች ለሚያስፈልጋቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የቤት እንስሶች ያቀርባል።
 Mobile spay/neuter clinic for pets
 የአካባቢ ጥበቃ   የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የባትሪ ኃይል መሙያዎች ($200,000)

ቦታ: በሂደት በሚወሰኑ የከተማዋ 3 ቦታዎች ላይ የሚሠሩ 10 የባትሪ ኃይል መሙያዎች።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (EV) ባትሪ መሙያ ጣቢያዎችን በከተማዋ 3 ቦታዎች ላይ የሚሠሩ ሲሆን፣ 10 የባትሪ ኃይል መሙያዎችን ይዘውም ይሠራሉ። የEV ተሽከርካሪዎች ብዛት ቀስበቀስ እየጨመረ መሆኑን በከተማው ውስጥ ከሚገኙ ባትሪ መሙያ ጣቢያዎች አስተዳደሩ የሰበሰበው መረጃ ያመላክታል። ይህ የፕሮጀክት ሃሳብ ተጨማሪ ለሕዝብ ተደራሽ የሆኑ የEV ባትሪ መሙያ ጣቢያዎችን እንደሚፈልጉ ያመላከቱ ነዋሪዎች ላነሱት ጠንካራ ጥያቄ ምላሽ ይሰጣል።
 Electric vehicle charger at Fresh Pond
መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል አስቸጋሪ የሆኑ እቃዎችን የሚሰበሰብ ተንቀሳቃሽ ማዕከል ($75,000)

ቦታ: በከተማው ዙሪያ እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።

እቃዎችን ይዘው መልሶ ጥቅም ላይ ወደሚያውላቸው ማዕከል ከመጓዝዎ ይልቅ ማዕከሉ ወደ እርስዎ ይምጣልዎ! በማኅበረሰብ ዝግጅቶች ወቅት ይህ ተንቀሳቃሽ ማዕከል የከተማዋ ነዋሪዎች እቃዎችን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል ከተማዋን መሻገር ሳይኖርባቸው መልሰው ጥቅም ላይ ማዋል እንዲችሉ ይረዳቸዋል። ኤሌክቶኒክ ቆሻሻዎችን፣ መጽሓፍቶችን፣ ባትሪዎችን፣ ፕላስቲኮችን እና ሌሎችንም መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል እገዛ ያቀርባል።
 DPW truck with a bed, likely one that will be used during recycling events.
የአካባቢውን አበባዎች ለማርባት ዘር በመበተን አስተዋጽዖ ለሚያደርጉ እንስሳት የሚሆን የአበባ ቦታ መገንባት ($75,000)

ቦታ: በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት እና ተጽዕኖ ዙሪያ የሚደረጉ ግምገማዎችን መሠረት በማድረግ የሚወሰን ይሆናል።

የአካባቢውን አበባዎች ለማርባት ዘር በመበተን አስተዋጽኦ ለሚያደርጉ እንስሳት የሚሆኑ የአበባ ቦታዎች በውስጣቸው፣ ለአካባቢው የድር እንስሳት የሚሆኑ ዘሮችን የሚያቀርቡ በአካባቢው የሚበቅሉ የእፅዋት ዝርያዎችን ይይዛሉ። ይህ ፕሮጀክት የአካባቢውን አበባዎች ለማርባት ዘር በመበተን አስተዋጽኦ ለሚያደርጉ እንስሳት የሚሆን የአበባ ቦታን በከተማዋ መናፈሻ ላይ በመገንባት፣ በአካባቢው የሚገኙ ዘር በታኝ እንስሳዎችን ለመሳብ እና ለመመገብ ይጠቅማል!
 Pollinator garden at Watson Street Lot
ስለት ላላቸው እቃዎች የሚሆኑ ደኅነታቸው የተጠበቁ ቆሻሻ መጣያዎች መሥራት ($30,000)

ቦታ: ከፍተኛ ፍላጎት በሚኖርባቸው ስድስት ቦታዎች ላይ እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።

ትልቅ እና ትንሽ መርፌዎችን ወይም ሌሎች ስለታም የሕክምና መሣሪያዎችን ደኅንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ ለማስወገድ የሚያስችሉ ቆሻሻያ መጣያ ሳጥኖችን መሥራት። እነዚህ የቆሻሻ ሳጥኖች በከተማው ውስጥ ከፍተኛ ፍላጎት በሚኖርባቸው ቦታዎች ላይ ስለት ያላቸውን ዕቃዎች ይበልጥ ደኅንነቱ በተጠበቀ እና ምቹ በሆነ የማስወገጃ አማራጮችን ያቀርባል።
 Sharps disposal box on Green Street
የመገልገያዎች፣ መናፈሻዎች እና መዝናኛዎች  Cambridge ውስጥ አዝናኝ መጫወቻ ቦታዎችን መሥራት ($150,000)

ቦታ: በመላው Cambridge ከተማ እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።

ለCambridge ሕፃናት የሚሆኑ አዝናኝ መጫወቻ ቦታዎችን እንገንባ! አካላዊ እንቅስቃሴ የተቀላቀለበት ጨዋታ ሕፃናት በቅርብ ክትትል ውስጥ ሆነው እየተጫወቱ መዝናናት እንዲችሉ ያድርጋል። የማኅበረሰቡ አጋር የሆኑ አገልግሎት አቅራቢዎች በሚያዘጋጇቸው ዝግጅቶች እና ሥልጠናዎች አማካኝነት የሕፃናት አዕምሮ ዓይነ-ህሊናን (ኢማጅኔሽን) የሚያሳድ አዲስ ዓይነት የመጫወቻ ቦታ (ጨዋታ) ይዘጋጃል።
 Adventure play in Costa Rica
ጥላ ሊሆኑ የሚችሉ ግንባታዎችን እና መቀመጫ የሚሆኑ ወንበሮችን በመገንባት መናፈሻዎችን ማሻሻል ($250,000)

ቦታ: በከተማው ዙሪያ በሚገኙ መናፈሻዎች።

ከፀሃይ ወይም ከዝናብ ሊከላከሉ የሚችሉ አንድ ወይም ሁለት መጠለያ ያላቸው መቀመጫዎችን በመገንባት መናፈሻዎችን እና የውሻ ማናፈሻ ሥፍራዎችን ለጎብኚዎች ምቹ ማድረግ። ይህ ፕሮጀክት በከተማው ውስጥ ባሉ የተለያዩ መናፈሻዎችም ውስጥ ተጨማሪ ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች እንዲገነቡ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል።
 Shaded seating in a Cambridge park
ትልቅ እናልም፦ የሕዝብ የSTEAM ፕሮግራሞች ($15,000)

ቦታ: በCambridge የሕዝብ ቤተ መጻሕፍቶች ውስጥ እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።

በአከባቢው ከሚገኙ የሥነ-ፈለክ እና STEAM ተቋማት ጋር በአንድ ላይ በመሆን በCambridge Public Libraries ውስጥ በምሽት ሰማይ ላይ ስለሚታዩ አስገራሚ እና አስደናቂ ነገሮች የሚያስተምሩ የሥነ-ፈለክ እና STEAM ፕሮግራሞችን እንደግፍ።
 Image of Dr. Cecilia Payne-Gaposchkin
በከተማው መናፈሻዎች የሚሰጡ ነፃ የፀሐይ መከላከያ ቅባቶች ($20,000)

ቦታ: በከተማው መናፈሻዎች ለሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።

በከተማው መናፈሻዎች እና መጫወቻ ቦታዎች ላይ ነፃ ከፀሃይ የሚከላከይ ቅባት ማከፋፈያ ማሽኖችን በመትከል Cambridge ጤናማ ሆና እንድትቆይ፣ የጨዋታ እና መዝናኛ ሰዓታችንም እንዲራዘም ያድርጉ! ይህ ፕሮጀክት የማከፋፈያ መሣሪያ ተከላ ሥራዎችን እና በቀጣይነት የሚያስፈልጋቸውን የጥገና ሥራ ለሦስት ዓመት በገንዘብ ይደግፋል።
 Sunscreen dispenser for parks
የትራንስፖርት፣ መንገዶች እና የእግረኛ መንገዶች   ለሕዝብ ዝግጅቶች በቀላሉ ተደራሽ የሆኑ ምንጣፎች ($20,000)

ቦታ: በከተማው ውስጥ ከቤት ውጪ ለሚዘጋጁ ዝግጅቶች እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።

Cambridge ውስጥ በየዓመቱ ብዙ ከቤት ውጪ የሚዘጋጁ ዝግጅቶች አሉ። ለእንቅስቃሴ ምቹ ተደርገው የሚዘጋጁ ምንጣፎች ወጣ ገባ በሆኑ መሬቶች ላይ በመነጠፍ፣ እነዚህ ዝግጅቶች የሚዘጋጁባቸውን ውብ አረንጓዴ ሥፍራዎች ተጨማሪ ሰዎች ማየት እንዲችሉ ዕድሉን ይከፍታሉ። እነዚህ ምንጣፎች የሕፃናት ጋሪዎች፣ ተሽከርካሪ ወንበሮች እና ሌሎች የእንቅስቃሴ ድጋፍ የሚሰጡ መሣሪያዎች የሚጠቀሙ ቤተሰቦችን ይደግፋሉ።
 Accessible mat for grassy/unpaved areas
ለአዋቂዎች የሚሆኑ አዝናኝ፣ ትምህርታዊ የብስክሌት ዝግጅቶች ($110,000)

ቦታ: በሕዝብ መናፈሻዎች፣ ባዶ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች፣ በብስክሌት መንገዶች ላይ እስከ 2 ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።

ለአዋቂዎች የሚሆኑ የብስክሌት ግልቢያ መማሪያ እና የከተማ ውስጥ የብስክሌት ግልቢያ መሠረታዊ እውቀት ማስጨበጫ ወክሾፖችን በማቅረብ የከተማዋን የብስክሌት ደኅንነት ትምህርት አማራጮች ማስፋት። ተጨማሪ የትምህርት ዕድሎች መኖራቸው፣ በከተማዋ ውስጥ ብስክሌት መጋለብ የሚያስችል ደኅንነት እንዳለ ተሰምቷቸው ተጨማሪ ሰዎች መጋለብ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል።
 Cyclists in Cambridge
ደኅንነታቸው የተጠበቁ ጎዳናዎች እንዲኖሩን ፍጥነት መቀነስ ($250,000)

ቦታ: ከአውራ ጎዳናዎች ጋር በመስቀለኛ በሚገናኙ ንዑስ መንገዶች።

የተሽከርካሪዎችን ፍጥነት ለመቀነስ 48 ፍጥነት መቀነሻ ጉብታዎችን ቁልፍ በሚባሉ የCambridge ጎዳናዎች ላይ መገንባት። ፍጥነት የሚቀንሱ ጉብታዎች የእግረኞችን ደኅንነት የሚጨምሩ ሲሆን፣ ለኑሮ ምቹ እና ደኅንነታቸው የተጠበቁ መኖሪያ ስፍራዎችንም ለመፍጠር ያግዛሉ። ይህ ፕሮጀክት ከፍጥነት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን ለመፍታት እና አጠቃላይ የመንገድ ደኅንነትን ለማሻሻል ያለመ ነው።
 Speed hump on a residential street

Gold Star Pool (Gold Star መዋኛ ገንዳ) ላይ ሰርጓጅ ተሽከርካሪ ወንበሮች ($12,000)

ቦታ: በGold Star Pool።

ከእንቅስቃሴ ችግሮች ጋር የሚኖሩ ሰዎች በGold Star Pool ውስጥ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ሰርጓጅ ተሽከርካሪ ወንበሮችን መግዛት። እነዚህ ተሽከርካሪ ወንበሮች ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ መዝናኛ እና ማኅበረሰብ ተሳትፎ የነበረውን ተደራሽነት ይጨምራሉ።  

 Submersible wheelchair
ወጣቶች  የቅርጫት ኳስ ሜዳ ማሻሻያዎች ($350,000)

ቦታ: በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት እና ተጽዕኖ ዙሪያ የሚደረጉ ግምገማዎችን መሠረት በማድረግ የሚወሰን ይሆናል።

ከቤት ውጪ የሚገኙ የቅርጫት ኳስ ሜዳዎችን ማሻሻል! ይህ ፕሮጀክት በአካባቢው በሚገኙ ማሻሻያ በሚያስፈልጋቸው ቦታዎች ላይ የቅርጫት ኳስ ሜዳ የመሬት እድሳት ይሠራል፣ መስመሮችን እንደ አዲስ ይቀባል፣ በተጨማሪም ሜዳውን በሁሉም የዕድሜ ክልል ላይ ያሉ ሰዎች መጠቀም እንዲችሉ ከፍ ዝቅ የሚል የቅርጫት ኳስ ቀለበት ይገጥማል።
 Basketball court in Cambridge
ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክለቦች የሚውል የገንዘብ ድጋፍ ($150,000)

ቦታ: በCambridge Rindge and Latin ትምህርት ቤት እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።

በCRLS የሚገኙ የተማሪ ክበቦች በአሁኑ ጊዜ ለማኅበረሰባችን ብዙ ጥሩ ነገሮችን ያደርጋሉ፦ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ አጋዥ ትምህርት፣ ትምህርታዊ እና ሙያዊ ማጎልበቻ ፕሮግራሞች እና ሌሎችንም ያደርጋሉ። እነዚህ ክለቦች ለማኅበረሰቡ እና ከዚህም አልፈው ለሚገኙ ሰዎች ሊያበረክቱ የሚችሉትን መልካም ነገሮች የሚያሳድግ አቅም እንዲኖራቸው የገንዘብ ድጋፍ እናቅርብላቸው!
 CRLS students at a public event with their student club.
የሴት ሕፃናት አቅም ማጎልበቻ ስፖርታዊ ዝግጅቶች ($45,000)

ቦታ: በWar Memorial፣ Danehy Park፣ በCPS ትምህርት ቤት ጂምናዚየሞች እና በሌሎች ቦታዎች ላይ እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።

የCambridge Sports for Girls Night በአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ ሴት ሕፃናት የሚሆኑ በርካታ ዝግጅቶችን እንዲያካትት ማድረግ። እነዚህ አዝናኝ ዝግጅቶች ሴት ሕፃናት ወይም ወጣቶች የማኅበረሰብ ድጋፍ በሚያገኙበት መቼት ውስጥ የተለያዩ ስፖርቶችን መሞከር እንዲችሉ ያደርጋሉ!
 Girls playing basketball at Sports Night for Girls

የMoses Youth Center ማሻሻያ ($150,000)

ቦታ: Moses Youth Center

በMoses Youth Center ላይ የማሻሻያ ሥራዎች እንሥራ! ይህ ፕሮጀክት በመላው የወጣት ማዕከሉ አዲስ እና ምቹ የሆኑ የማዕከል እቃዎች (ፈርኒቸሮች) ያስገባል፣ የጂምናዚየሙ መጋዘን ለተንቀሳቃሽ መሣሪያዎች የተሻለ ምቾት እንዲኖረው ያደርጋል፣ በተጨማሪም ወጣቶች ሊጠቀሙበት የሚችሉት አዲስ የሙዚቃ ስቱዲዮ ይገነባል።  

 Moses Youth Center

 

 

.

 

 


Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here