U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

የከተማው አስተዳዳሪ መልዕክት

ሰኞ ፣25 ሴፕቴምበር 2023
" የአየር ንብረት ለውጥ በሕይወታችን ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው እናም ለከተማው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። እንደ ማህበረሰብ፣ ይህንን ወሳኝ ስራ ለማሳካት በአስቸኳይ እርምጃ መውሰድ እና ቁርጥ ውሳኔ ማድረግ አለብን።  በዚህ ሥራ ውስጥ እንደ መሪ፣ ሰፋ ያሉ ግቦችን አውጥተናል እናም በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሁሉም ጠቃሚ ሚና ለመጫወት እድሎች አሏቸው ።  "

ውድ የካምብሪጅ ማህበረሰብ ፣ 

የአየር ንብረት ለውጥ የእኛ ትውልድ ትግል ነው ። ዜናውን ሳነብ፣ ሳይንቲስቶቻችን እኛ ከምናውቀው በላይ እየጨመረ የሚሄደውን ማንቂያ ሲገልጹ ብቻ የበለጠ እጨነቃለሁ ። በፕላኔታችን ላይ የአለም ሙቀት መጨመርን የሚያፋጥኑ ተፅእኖዎችን አስቀድመን እያየን ነው – ከፍተኛ ሙቀት ፣ ጭሳቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ማይሎችን ርቆ የሚሄድ ግዙፍ የሰደድ እሳት እና ከተማዎችን በጎርፍ ሚያጥለቀልቁ ኃይለኛ አውሎ ንፋሶች። ተለዋዋጭ የአየር ንብረታችን በዓለም ዙሪያ በጣም ተጋላጭ የሆኑትን ብቻ ሳይሆን፣ በካምብሪጅ ውስጥም በአካባቢያችን ላይም ተጽዕኖ ያሳድራል ። በቀጣዮቹ አስርት ዓመታት የምናደርገው ነገር ለልጆቻችን እና ለሚቀጥለው ትውልድ የምንተወውን ዓለም አቅጣጫ ያስቀምጣል። 

የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመቅረፍ ኢኮኖሚያችንን እና መሠረተ ልማታችንን በከፍተኛ ሁኔታ ማዋቀርን የሚጠይቅ ሲሆን በፌዴራልም ሆነ በስቴት ደረጃ ጉልህ እርምጃዎችን እያየን እንደሆነ ተስፋ ይሰጠኛል ። የፌደራል የዋጋ ግሽበት ቅነሳ ህግ ከ 500 ቢሊዮን ዶላር በላይ የአየር ንብረት ኢንቨስትመንቶችን እያደረገ ሲሆን ስቴቱ የታዳሽ ኃይል ማመንጫን ለማሳደግ እና የኃይል አጠቃቀምን መንገድ የሚቀይር የግሪድ መሠረተ ልማትን ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው። ነነገር ግን አብዛኛው አስፈላጊ ለውጥ እንዲሁ አካባቢያዊ ይሆናል – እንደ ከተሞች አኗኗራችንን፣ አሰራራችንን እና ጉዞያችንን ለመለወጥ እኛ የሚንሰራው 

የካምብሪጅ ከተማ ለብዙ ዓመታት የአየር ንብረት መሪ ሆና ከከተማው ምክር ቤት ፣ ከአየር ንብረት ተሟጋቾች እና ከባለሙያዎች ፣ ከንግድ እና ከተቋማዊ መሪዎች እና ነዋሪዎች ጋር በቅርበት ሰርታለች ። በ 2015 የNet Zero የድርጊት መርሃ ግብር ተቀባይነት አግኝቶ ቅድሚያ በተሰጣቸው የአየር ንብረት መርሃግብሮች እንድንሄድ ያደርገናል። በዚህ ባለፈው ሰኔ ፣ የተሻሻለው የሕንፃ ኃይል አጠቃቀምን ይፋ የማድረግ ድንጋጌ (BEUDO) በማፅደቅ ትልቅ ምዕራፍ አልፈናል፣ ይህም ትልልቅና መኖሪያ ያልሆኑ ሕንፃዎች በ2035  የnet zero መስፈርት የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀታቸውን እንዲቀንሱ ያስገድዳል። የ BEUDO ሕንፃዎች ~60% የከተማውን ልቀቶች ይወክላሉ እናም ይህ ደንብ በ 2035 በ BEUDO ልቀቶች 70% ቅናሽ ላይ ያነጣጠረ ሲሆን ይህም በአገሪቱ ውስጥ በጣም ጠንካራ የከተማ ግብን ይወክላል ። ከነሐሴ 2023 ጀምሮ፣ በእንዲሁም በአዲስ ግንባታ ወይም በትላልቅ እድሳት ላይ የቅሪተ አካል ነዳጅ አጠቃቀምን የሚገድብ አዲስ ከቅሪተ አካል ነፃ ደንብ አዘጋጅተናል። እንዲሁም የህዝብ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል መሙያ ጣቢያዎችን አስፋፍተናል ። 

ይህ የካምብሪጅ ላይፍ እትም እነዚህን ዋና ዋና ተነሳሽነት እንዲሁም በመላው ከተማ እየተከናወኑ ያሉ ሌሎች የአየር ንብረት ሥራዎችን አጠቃላይ እይታን ይሰጣል ። እንዲሁም ከተማው ነዋሪዎችን እና ንግዶችን ለመደገፍ ምን እያደረገ እንደሆነ ፣ ድምጽዎን እንዴት ማሰማት እንደሚችሉ ፣ እና ለውጥ ለማምጣት ሊወስዷቸው ስለሚችሏቸው እርምጃዎች ይማራሉ–ለካምብሪጅ ማህበረሰብ ኤሌክትሪክ 100% ታዳሽ ኤሌክትሪክ ፕሮግራም መመዝገብም ወይም የከተማውን የነፃ ኮምፖስቲንግ ፕሮግራም በመጠቀም። ስለ ከተማዋ የአየር ንብረት ስራ እና እንዴት መርዳት እንደሚችሉ የበለጠ ለማወቅ፣ www.cambridgema.gov/CDD/Climateandenergy ን ይጎብኙ። ነዋሪዎች ስለዚህ ስራ በከተማው ውስጥ ካለ ሰው ጋር መገናኘት ከፈለጉ፣ በ Climate@cambridgema.gov ላይ ኢሜይል እንዲልኩ ይበረታታሉ 

በአለም አቀፍ ደረጃ ወሳኝ ነጥብ ላይ ደርሰናል እናም በሠራነው ሥራ ኩራት ቢሰማኝም፣ ብዙ መስራት ያለብን ስራዎች አሉ። በማንኛውምሥራችን ፣ እንደ ማህበረሰብ አብረን ወደፊት እንጓዛለን ። 

ከሰላምታ ጋር፣ 

Yi-An Huang 

Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here