ተጨማሪ ለማዳመጥ ጠቅ ያድርጉ
የኔቲቭ አሜሪካዊያን ቦታዎች
ማኅበረሰቡ ነጮች እዚህ መጥተው ከመስፈራቸው በፊትም ሆነ በኋላ ኔቲቭ ሕዝቦች እዚህ መሬት ላይ መኖር መቀጠላቸውን የሚያሳዩ የቦታ መለያዎች እና ምልክቶች እንዲቋቋሙ ገንዘብ በማሰባሰብ እና ነዋሪዎችን እና ጎብኚዎችን ስለ ኔቲቭ ሕዝቦች ሕይወት እና ወግ ግንዛቤ እንዲጨብጡ በማድረግ በCambridge ውስጥ ለነባር (ኢንዲጂኒየስ) ሕዝቦች የሚሰጠውን እውቅና ለማስፋፋት በCambridge ከተማ አስተዳደር Participatory Budgeting (PB) ሂደት በኩል የድጋፍ ድምጹን ሰጥቷል። የዚህ PB ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ በEast Cambridge ውስጥ የሚገኙትን ባለቁጥር የመንገድ ስሞች ወደ Massachusett ቋንቋ መተርጎም እና አዲሶቹን የመንገድ ምልክቶች ከFirst እስከ Eighth ጎዳናዎች ድረስ መግጠም ነበር። ይህ ድር-ጣቢያ ፕሮጀክቱን ለማስተዋወቅ የሚውል ሲሆን፣ ወደፊትም ፕሮጀክቱ ላይ ለሚካተቱ አካላት እና ፕሮግራሞች እንደ መነሻ ሆኖ ያገለግላል።
የፕሮጀክት አመጣጥ
የEast Cambridge ነዋሪ እና የRhode Island Northern Narragansett ኔቲቭ አሜሪካዊ ጎሳ አባል በሆኑት Sage Carbone የቀረበ።
የ2021 ዓ.ም Participatory Budgeting ዑደት 8።
African American & Indigenous Peoples Reckoning Project (ከአፍሪካ አሜሪካዊ እና ነባር (ኢንዲጂኒየስ) ሕዝቦች ጋር የመታረቅ ፕሮጀክት) የCambridge ነዋሪዎች ድምፅ ሰጥተው ከመረጧቸው ሰባት ፕሮጀክቶች (ከሃያ ፕሮጀክቶች) መካከል አንዱ ነበር።
በእንግሊዝኛ እና በMassachusett የተጻፉ የመንገድ ምልክቶች
ዲዛይኑ፦
ወይን ጠጅ እና አረንጓዴ ቀለሞች ለምን ተመረጡ?
በMassachusett ቋንቋ ለሚጻፈው የምልክቱ ክፍል ወይን ጠጅ ቀለምን የመረጥንበት ምክንያት ኔቲቭ ሕዝቦች wampum ጨሌዎችን ለመስራት ከሚጠቀሙባቸው የquahog ክላም ሼሎች ቀለም ጋር ተመሳሳይ ስለሆነ ነው። አረንጓዴው ቀለም በብዙ ማዘጋጃ ቤቶች እና የአውራ ጎዳና መምሪያዎች ለመንገድ ማሳያ ምልክቶች ጥቅም ላይ ይውላል። አስፈላጊ የሆነ ቀለም ባይሆንም በቀላሉ ሊታወቅ የሚችል ነው። የቀለሞቹ አንፃራዊነት አንድን ነገር በተለያዩ መንገዶች መመልከት እንደምንችል ያስታውሰናል።
የነባር (ኢንዲጂኒየስ) ሕዝቦች ድምፆች
"ሰዎች በዚህ ሲያልፉ ወይም ሊጎበኙ ሲመጡ East Cambridge እና Kendall Square በታሪካቸው ለነበረው ኢ-ፍትሐዊነት እውቅና ለመስጠት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ይመለከታሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።"
Sage Carbone በኖቬምበር 3 ቀን 2023 ዓ.ም የWBZ ቃለ መጠይቅ ላይ የተናገሩት
"ሁልጊዜ ትንንሽ እርምጃዎችን እንፈልጋለን ምክንያቱም ልክ እንደ ህፃን ትንንሽ እርምጃዎች በስተመጨረሻ ወደ መሮጥ እና እንደምታውቁት ሌሎች ብዙ አይነት ትላልቅ ነገሮችን ወደ መሥራትም እንደሚያመሩ እናውቃለን።"
David Shane Lowry በኦክቶበር 9 ቀን 2023 ዓ.ም የWGBH ቃለ መጠይቅ ላይ የተናገሩት
በPonkapoag ስለሚገኘው የMassachusett Tribe ይወቁ
“የMassachusett tribe አሁን Commonwealth of Massachusetts በሚባለው ቦታ የእንግሊዝ ወራሪዎች መጀመሪያ ሲደርሱ ያገኟቸው የመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ዘር ናቸው። እኛ ብዙ ተዳሮቶች ቢኖሩብንም እንደ የመጀመሪያዎቹ የMassachusetts ሕዝቦች ሕልውናችንን ማስጠበቅ ችለናል። እንደ የMassachusett ሕዝብ ሕልውናችንን ማስቀጠል የቻልነው ቅድመ አያቶቻችን እንዳደረጉት ሁሉ በቃል የሚተላለፈውን ወግ ጠብቀን ስለቆየን ነው። ይህ ወግ የMassachusett ሕዝብ ስለ ዓለም ያለንን አመለካከት፣ ከተፈጥሮ ጋር ያለንን ግንኙነት እና ነገሮች አሁን ያሉበት ሁኔታ ላይ ያሉት በምን ምክንያት እንደሆነ ለትውልድ ያስተላልፋል። በማኅበረሰባችን ውስጥ ነገሮችን የምናስተውልባቸው እና የምናደርግባቸው ሺህ ዓመታትን ያስቆጠሩ መንገዶች አሉ። ከሺህ ዓመታት በፊት የነበሩ እና ዛሬም ድረስ የምንጠቀምባቸው የሕክምና መንገዶች አሉ። ማቆየት የቻሏቸውን ወጎች በማቆየታቸው፣ ለአርቆ አሳቢነታቸው፣ ትተውልን ላለፉት ስጦታዎች እና አሁንም ለሚሰጡን ትምህርት ቅድመ አያቶቻችንን እንዘክራለን።"
ስለ ፕሮጀክቱ የበለጠ ይወቁ
አስተያየትዎን ይስጡ
- የበጀት ጽሕፈት ቤት
- የካምብሪጅ ታሪካዊ ኮሚሽን
- የከተማው ሥራ አስኪያጅ ቢሮ
- ትራፊክ፣ መኪና ማቆሚያ እና መጓጓዣ
- የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ
- የቋንቋ ፍትሕ ክፍል
- ሥነ-ጥበባት እና ባህላዊ እቅድ አወጣጥ ቢሮ