U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

Participatory Budgeting

ማቅረብ የሚፈሉጓቸውን ሐሳቦች እዚህ ያስገቡ

Participatory Budgeting (PB) የማኅበረሰቡ አባላት ለማኅበረሰቡ የታቀደ በጀት ምን ላይ መዋል እንዳለበት መወሰን እንዲችሉ የሚያደርግ ዲሞክራሲያዊ ሂደት ነው። የCambridge ከተማ አስተዳደር PB ነዋሪዎች በከተማ አስተዳደሩ የበጀት አወጣጥ ሂደት ላይ እንዲሳተፉ እንደሚረዳቸው ተስፋ ያደርጋል። PB የዜጎችን ተሳትፎ እና የማኅበረሰቡን የአብሮነት መንፈስ ለማሳደግ እና በከተማው አስተዳደር በጀት ውስጥ የሚካተቱት ጉዳዮች የCambridge ነዋሪዎች ቅድሚያ የሚሰጡዋቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ለማረጋገጥ ታላሚ አድርጓል።

አሥራ አንደኛው የPB ምዕራፍ ተጀምሯል፣ ከተማውም እርስዎ በፕሮጀክቶች ዙሪያ ማቅረብ የሚፈልጓቸውን ሐሳቦች መስማት ይፈልጋል! የምንኖርበትን ማኅበረሰብ ለማሻሻል የተያዘውን የ1 ሚሊዮን ዶላር በጀት ምን ላይ ማዋል ይፈልጋሉ?

ለፉት የPB ምዕራፎች አሸናፊ ከሆኑ ፕሮጀክቶች ውስጥ የተወሰኑት የወጣቶች ማዕከል የማሻሻያ ሥራ፣ በቅርቡ መኖሪያ ቤት ላገኙ ነዋሪዎች የቤት ዕቃ የማቅረብ ሥራ፣ ለ Main Library የሶላር ፓነሎች የመግጠም ሥራ፣ በሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የልብስ ማጠቢያ ማሽን አቅርቦት እንዲኖር የማድረግ ሥራ እና ሌሎችንም ያካትታሉ!

ማቅረብ የሚፈልጓቸውን ሐሳቦች ከኦክቶበር 1 ቀን 2024 ዓ.ም በፊት ያስገቡ።

የPB11ኛ ምዕራፍ የአፈጻጸም መርሃ-ግብር፦

  • ሴፕቴምበር፦ ማቅረብ የሚፈልጓቸን ሐሳቦች ያስገቡ!
  • ከኦክቶበር 2024 እስከ ፌብሩዋሪ 2025 ዓ.ም፦ የከተማው በጎ ፈቃደኛ ነዋሪዎች የቀረቡ ሐሳቦችን መርምረው እነዚህን ሐሳቦች ያካተተ የፕሮጀክት ዕቅድ ያዘጋጃሉ። የከተማው ሥራ አስኪያጅ እና የከተማው አስተዳደር ሠራተኛዎች ለPB የምርጫ ሂደት የሚቀርቡ 20 ዕቅዶች ያጸድቃሉ።
  • ማርች 2025 ዓ.ም፦ የPB ምርጫ ይጀምራል! Cambridge ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች የዜግነት ሁኔታቸው ምንም ሆነ ምን ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት እና ከዚያ በላይ ከሆነ በምርጫ ሂደቱ ላይ መሳተፍ ይችላሉ።

Cambridgeን ለማሻሻል ሐሳብ ማጋራት ከፈለጉ እዚህ ጋር ጠቅ ያድርጉ!

Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here