U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

የትራንስፖርት ተጠቃሚ እና የአካባቢ ጥበቃ መሐንዲስ ሲዋሃዱ፦ የPublic Works ሠራተኛ Diane Stokes ታሪክ

ረቡዕ ፣4 ዲሴምበር 2024
" በምህንድስና እና የጎዳናዎች እና የፍሳሽ ማስወገጃ ጥገና መካከል ያለውን ክፍተት ማጥበብ የሚያስችል ሚና ስላለኝ ያስደስተኛል "

የCambridge ነዋሪ እና የአካባቢ ጥበቃ መሐንዲስ የሆኑት Diane Stokes ከቀን ወደ ቀን ሴት ልጃቸውን ትምህርት ቤት ለማድረስ እና ለመመለስ Massachusetts Avenue ላይ ብስክሌት ሲነዱ አስበውበትም ሆነ ሳያስቡበት በጉዟቸው ላይ የሚያጋጥሟቸውን አስቸጋሪ ነጥቦች ያስተውሉ ነበር። ነገሮችን ትንትኖ የመመልከት ችሎታ ያለው አስተሳሰባቸው እና በመስኩ ያካባቱት እውቀት በዚህ ወሳኝ የከተማ መንገድ ላይ ያሉትን ጥቃቅን ችግሮች እንኳን በሚገባ እንዲገነዘቡ አስችሏቸዋል።

ከMemorial Drive ጀምሮ እስከ Alewife Brook Parkway ድረስ Cambridgeን የሚያቋርጠው የ3.5 ማይል ርዝመት ያለው Massachusetts Avenue ብዙ ነዋሪዎች ሳይወዱ በግዳቸው በተላመዷቸው ከትራንስፖርት ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶቹ የታወቀ ነው። ሆኖም በወጣትነት ዕድሜያቸው Harvard Square ውስጥ የባንክ ሠራተኛ ሆነው እያገለገሉ በነበረበት ጊዜ እና አሁንም ልጃቸውን ትምህርት ቤት በሚያመላልሱበት ጊዜ Mass Ave ላይ ሲጓዙ የቆዩት Stokes ጎዳናው ላይ በሚደረገው ለውጥ ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።

Stokes በDepartment of Public Works (DPW) የምህንድስና አገልግሎት ዳይሬክተርነት ሚናቸው ከመነሻው ጀምሮ የCambridge’s Mass Ave ከፊል ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ላይ ያሉትን የምህንድስና ዲዛይን ጥረቶች ሲመሩ ቆይተዋል። ይህ ፕሮጀክት እ.ኤ.አ በ2019 ዓ.ም Cycling Safety Ordinance ድንጋጌዎች መሠረት በመንገዱ ዳር የሚገኙ የአካባቢው የንግድ ሥራዎችን እየደገፈ ሁሉንም የትራንስፖርት አማራጮች ማስተናገድ የሚችል የመንገድ መሠረተ ልማት ለመፍጠር ያልማል።

በPublic Works ኮሚሽነር Kathy Watkins እይታ ይህ ፕሮጀክት የሚጠብቀውን ከባድ ሥራ ወደፊት እንዲያራምዱ Stokesን መሾም ግልፅ እና አስተማማኝ የሆነ ምርጫ ነበር። የአካባቢው ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ ከመሆናቸው አንፃር የሚያገኙት አመለካከት እና ሁለገብ የሆኑ ትላልቅ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ያላቸው ልምድ Stokesን ተመራጭ እጩ ያደርጋቸዋል።

ታዋቂ የሆኑባቸውን የሥራ ጫማዎች፣ የሥራ ሱሪ እና የቦሄሚያ ሻሽ ለብሰው የሚታዩት Stokes ለምህንድስና እና ተያያዥ ለሆኑት በርካታ ፈተናዎቹ ያላቸው ፍቅር ሊገራ የማይችል ነው። Stokes እ.ኤ.አ በ2014 ዓ.ም የCambridgeን DPW ቡድን ከተቀላቀሉ በኋላ የዝናብ ውኃ መሙላት እና የጎርፍ መጥለቅለቅ ችግሮችን ለመፍታት በተጀመረው የከተማ አስተዳደሩ የWestern Avenue መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት ላይ ወዲያውኑ መሳተፍ ጀምረዋል። ፕሮጀክቱ በCambridge ውስጥ ሌላኛው ቁልፍ ዋና መንገድ የሆነው Western Avenueን አፈጻጸም፣ ደኅንነት እና ውበት ለማሳደግም ያለመ ነበር።

"አሁን የብስክሌት መንገዱ ላይ [Western Ave. በሚገኘው] ብስክሌት እየነዳሁ ባለፍኩ ቁጥር የአስፓልቱ ንጣፉ ያለበትን ሁኔታ እያስተዋልኩ እና Riverside Placeን እየታዘብኩ ነው የማልፈው" Riverside Place ከWestern Ave አለፍ ብሎ የሚገኝ ለዝናብ ውኃ ማስወገጃ ሙሌቶች ተጋላጭ የሚያደርጉ ባህሪያት ያሉት አጭር፣ ጠባብ እና ጠፍጣፋ አሠራር ያለው መውጫ የሌለው ጎዳና ነው። የዝናብ ውኃ ተፋሰስ ማስወገጃዎቹ ፈሳሽ ውኃ መቀበል እንዲችሉ በመጠነኛ ተዳፋት መንገዱ መሃል እንዲቀመጡ ተደርጎ ዲዛይኑ ተለውጧል። “የሚገርመው አሁን እየሠሩት ላለው አንዳንድ የጋራ የመንገድ ዲዛይኖች ላይ ከግምት ውስጥ እየገባ ነው፤ እና ያ በጣም የሚያረካ ነው።”

የMas Ave ከፊል ግንባታ ፕሮጀክት በተጀመረበት ጊዜ Stokes ከቦታ ቦታ ለመጓጓዝ Mas Aveን እየተጠቀሙ በርካታ ዓመታትን አስቆጥረው ነበር። በMass Ave ላይ ያለው የአውቶቡስ እንቅስቃሴ ለእርሳቸው የዕለት ተዕለት መርሃ ግብር አስተማማኝ አለመሆኑን ቀድመው ተረድተው ስለነበር በዋናነት በእግር መራመድን እና ብስክሌት መንዳትን እንዲመርጡ እና የመኪናቸውን አጠቃቀም እንዲቀንሱ ተገድደው ነበር፤ ፕሮጀክቱ ለመፍታት ከሚፈልጋቸው ችግሮች መካከል አንዱ ይህ ነው። Stokes ብስክሌት እየነዱ የተነጠሉ የብስክሌት መስመሮች በሌሉበት የMass Ave ጎዳና ሲጓዙ የደኅንነት እጥረት እንዳለባቸው የተሰማቸውን ቦታዎች ለይተዋል።

Stokes ለፕሮጀክቱ ባደረጉት ዝግጅት በሁሉም የቀኑ ሰዓታት ላይ ያለውን የMass Ave የትራፊክ እንቅስቃሴ ለመመልከት ሆን ብለው መኪናቸውን ይበልጥ መጠቀም ጀመሩ። ይህ ልምምድ መራዘም ያለባቸው ወደ ግራ መታጠፊያ የመንገድ መስመሮች የሚገኙባቸው ቦታዎችን፣ በብስክሌቶች እና ወደቀኝ በሚታጠፉ ተሽከርካሪዎች መካከል ትላልቆቹ ግጭቶች የሚፈጠሩባቸው ቦታዎችን እና በተደጋጋሚ የሚሻገሩ እግረኛዎች በመኖራቸው ተጨማሪ የእግረኛ መሻገሪያ የሚያስፈልጋቸው ቦታዎችን የመሳሰሉ የማነቆ ነጥቦችን ለይተው መጠቆም እንዲችሉ አስችሏቸዋል።

በመሆኑም ለፕሮጀክቱ መነሻ ያላቸውን ግንዛቤ እንዲያካፍሉ ከWatkins ጥያቄ ሲቀርብላቸው ዝግጁ የነበሩት Stokes በፕሮጀክቱ አካባቢ በመጓጓዝ ያገኙትን ተሞክሮ መሠረት በማድረግ ማሻሻያ ሊደረግባቸው የሚችሉ አካባቢዎችን በፍጥነት ለይተው ጠቆሙ።

የመጀመሪያዎቹ የፕሮጀክት ስብሰባዎች ይበልጥ በመንገድ ዲዛይን ላይ ያተኮሩ እንደነበሩ የሚናገሩት Stokes የፕሮጀክቱ ቡድን የፕሮጀክቱን ፍላጎቶች በደንብ ተረድቶ ጥረቶቹን አቅጣጫ ማስያዝ እንዲችል የእርሳቸው "የተጠቃሚ አመለካከት" መርዳቱን ይገልጻሉ። ለማዘጋጃ ቤት ምህንድስና ጥልቅ ፍቅር ያላቸው Stokes የከርሰ ምድር መሠረተ ልማትን መገምገም እና አሁን ካለው ነባራዊ የከርሰ ምድር ሁኔታ አንፃር የምድር ገጽ ላይ ሊገነባ የሚችል ዲዛይን ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። "በምህንድስና እና የጎዳናዎች እና የፍሳሽ ማስወገጃ ጥገና መካከል ያለውን ክፍተት ማጥበብ የሚያስችል ሚና ስላለኝ ያስደስተኛል" ሲሉ Stokes ይናገራሉ።

በከተማው ውስጥ ብዙ የተለያዩ እና ተፎካካሪ የሆኑ አጣዳፊ ጉዳዮች መኖራቸውን ያመኑት Stokes “… ፕሮጀክቱን በምዕራፎች ከፋፍለን የምናካሂድበት መንገድ እና በተከታታይ የበጀት ዓመታት ውስጥ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኝበት መንገድ ላይ በጥልቀት ማሰብ አለብን።" የግንባታው የመጀመሪያ ምዕራፍ በዋነኛነት በRoseland Street እና Waterhouse Street መካከል በሚገኙ መገልገያዎች ላይ የሚደረግ ጥገና እና በዚሁ መንገድ ላይ ያሉ ሌሎች የጥገና ሥራዎች ዙሪያ ያተኩራል። የግንባታ ጨረታ ጥቅል እየተዘጋጀ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2025 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ የግንባታ ሥራ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

Stokes በDPW ፕሮጀክቶች ላይ ያላቸው ተጽእኖ በስፋት እየታወቀ ሲመጣ ጎረቤቶች እና ሌሎች የማህበረሰብ አባላት በCambridge ዙሪያ ያሉ ከትራንስፖርት ደኅንነት ጋር የተያያዙ ስጋቶችን ይዘው ወደ እርሳቸው መቅረብ ጀመሩ። የStokes ምልከታዎች እና የማኅበረሰብ ተሳትፎ እንቅስቃሴዎች በከተማው ውስጥ የሚሰሩ እና የሚኖሩ ሠራተኞች ያላቸውን ጠቀሜታ አጉልቶ ያሳያል፤ ምክንያቱም ነዋሪዎች ያላቸው ቀጥተኛ ተሞክሮ እና በርካታ የግንኙነት ነጥቦች የለውጥ ፕሮጄክቶች የማስፈጸም ችሎታቸውን በእጅጉ ያሳድጋል።

“ትልቅ የውይይት ነጥብ ነው” በማለት ይናገራሉ። “የዛሬን ችግሮች እየፈታን ብቻ ሳይሆን 25 እና 100 ዓመታትም ጭምር ወደፊት አርቀን እያሰብን ነው። ይህንን ለቀጣዩ ትውልድ እየገነባን ነው።"

Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here