U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

ከባድ አደጋዎችን ተከትሎ የሚተገበሩ አሠራሮችን የማሻሻል ሥራ

ረቡዕ ፣4 ዲሴምበር 2024

Cambridge ውስጥ Vision Zero ተግባራዊ መደረግ ከጀመረበት እ.ኤ.አ 2016 ዓ.ም አንስቶ የከተማ አስተዳደሩ የሞት መንስዔ ለሆኑ የትራፊክ አደጋዎች ምላሽ የሚሰጥበትን አሠራሮች አስቀምጧል። ከሞት አደጋ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በመላው ከተማ ከሚገኙ መምሪያዎች የተውጣጡ ባለብዙ መስክ ሠራተኞችን የያዘ ቡድን አደጋው የደረሰበትን ቦታ በመጎብኘት ጊዜያዊ እና ዘላቂ ማሻሻያ ማድረግ የሚቻልባቸውን ዕድሎች ይገመግማል። ለምሳሌ የሞት አደጋ ያስከተሉ ግጭቶችን ተከትሎ በHarvard Square ላይ የተተገበሩት ጊዜያዊ ማሻሻያዎች በHarvard Yard እና Out of Town News Kiosk መካከል Mass Ave ላይ በቅልጥፍና የተገነቡ የተነጠሉ የፈጣን ልማት ብስክሌት መስመሮችን እና ከካፒታል ግንባታ ፕሮጀክቶች ቀደም ብሎ የተከናወነ COOP ፊት ለፊት የሚገኘው የMass Ave የመኪና መንገድን የማስወገድ ሥራዎች ይካተታሉ። በInman Square የተፈጠረው ሞትን ያስከተለ ግጭት የመላው አደባባዩን ዲዝይን ማሻሻያ እና መልሶ ግንባታ ሥራ ያፋጠነ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩም በአካባቢው ላይ ወደ 10.4 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት አድርጓል። የተሠራው ሥራ በመላው አካባቢ የተገጠመ አዲስ የመንገድ መብራት ሥርዓትን፣ የትራፊክ ምልክት ሥርዓትን፣ የተደራሽነት ማሻሻያዎችን እና ሌሎች የመልሶ ግንባታ ማሻሻያዎችን ያካትታል።

በአሁኑ ወቅት የከተማ አስተዳደሩ ለሞት መንስዔ የሆኑ ግጭቶች የተፈጠሩባቸው ቦታዎች ላይ ግምገማ የማካሄድ ሂደትን መደበኛ የሚያደርግ እና የደኅንነት ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን መስቀለኛ መንገዶች ቀደም ብሎ የሚለይ፣ የሚመረምር እና ስጋቶችን የሚቀንስ የተሻሻለ የSafety Audit (የደኅንነት ኦዲት) ፕሮግራም ለመፍጠር እየሠራ ነው። ይህም የግጭት ታሪኮችን መገምገም፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን መስቀለኛ መንገዶችን ለይቶ መዘርዘር እና ቀጣይነት ያለው ማሻሻያ ለማድረግ ዕቅድ ማውጣትን ይጨምራል። በዚህ ጊዜ ማዕቀፉ ገና በመቀረጽ ላይ ያለ እና ለውጦች ሊደረጉበት የሚችል ነው። እ.ኤ.አ በ2024 ዓ.ም መኸር ወቅት ላይ ተጨማሪ መረጃ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

ለሥራው ቅድሚያ ለመስጠት በሚል የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች በከተማው ውስጥ ያሉ መስቀለኛ መንገዶች ያላቸውን የግጭት ታሪክ እየመረመሩ ነው። ጥናቱ መጀመሪያ ላይ አስፈላጊ ለውጦች ከውስጥ ማድረግ በሚቻልባቸው በከተማ አስተዳደሩ ባለቤትነት የተያዙ መስቀለኛ መንገዶች ላይ የሚያተኩር ይሆናል።

በድንበሮቻችን ውስጥ ከፍተኛ አደጋ ከሚፈጠርባቸው ቦታዎች መካከል በስቴት ባለቤትነት የተያዙ መስቀለኛ መንገዶች ይጠቀሳሉ። ነገር ግን እነዚህን ቦታዎች በከተማ አስተዳደሩ ባለቤትነት ከተያዙ ቦታዎች ለይተን እየመረመርን ሲሆን Memorial Driveን ጨምሮ በስቴት ባለቤትነት የተያዙ መንገዶች ላይ የደኅንነት ስጋቶችን ለመፍታት በትይዩ ጥረት ከስቴት ኤጀንሲዎች ጋር በጋራ እንሠራለን።

ለእያንዳንዱ የመስቀለኛ መንገድ ግምገማ የኦዲት ሂደቱን፣ ግኝቶችን፣ የሚመከሩ ማሻሻያዎች እና የትግበራ የጊዜ ሰሌዳዎች የሚያብራራ ቴክኒካዊ ማስታወሻ ተዘጋጅቶ ይቀርባል። የመጨረሻው ሪፖርት በከተማ አስተዳደሩ የVision Zero ድር-ጣቢያ ላይ ይታተማል።

ከተማ አስተዳደሩ የመኪና አደጋ መረጃዎችን የሚያመዛዝንበት እና ደረጃ የሚሰጥበትን ዘዴም በማሻሻል ላይ ይገኛል። ያልተቀናበረ መረጃ ምህ ያህል የመኪና አደጋዎች ሪፖርት ተደርገዋል ለሚለው ቀለል ያለ ምላሽ የሚያቀርብ ቢሆንም ተጋላጭ የመንገድ ተጠቃሚዎችን ተሳትፎ ወይም ጉዳት፣ የጉዳቱን ክብደት እና የከባድ መኪናዎችን ተሳትፎ ጨምሮ ምርመራ የሚደረግባቸውን ወሳኝ ነገሮች ከግምት ውስጥ አያስገባም።

Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here